ነገር ግን በየኰረብቶች ላይ የነበሩትን የአሕዛብ መሠዊያዎችን አላስወገደም፤ ሕዝቡም መሥዋዕት ማቅረባቸውንና ዕጣን ማጠናቸውን እንደ ቀጠሉ ነበር፤ የቤተ መቅደሱን ሰሜናዊ ቅጽር በር ያሠራ ይኸው ኢዮአታም ነበር።
ኤርምያስ 26:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የይሁዳ መሪዎችም የሆነውን ነገር በሰሙ ጊዜ ከቤተ መንግሥት ወጥተው ወደ ቤተ መቅደስ መጡ፤ በቤተ መቅደሱም በአዲሱ የቅጽር በር ስፍራቸውን ያዙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የይሁዳም ባለሥልጣኖች ስለ እነዚህ ነገሮች በሰሙ ጊዜ፣ ከቤተ መንግሥት ወደ እግዚአብሔር ቤት ወጡ፤ በእግዚአብሔር ቤት፣ አዲሱ በር በተባለው መግቢያ ተቀመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የይሁዳም አለቆች እነዚህን ነገሮች በሰሙ ጊዜ ከንጉሥ ቤት ወደ ጌታ ቤት ወጡ፥ በአዲሱም በጌታ ቤት ደጅ መግቢያ ተቀመጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የይሁዳም አለቆች ይህን በሰሙ ጊዜ ከንጉሡ ቤት ወደ እግዚአብሔር ቤት ወጡ፤ በአዲሱም በእግዚአብሔር ቤት ደጅ መግቢያ ተቀመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የይሁዳም አለቆች ይህን በሰሙ ጊዜ ከንጉሥ ቤት ወደ እግዚአብሔር ቤት ወጡ፥ በአዲሱም በእግዚአብሔር ቤት ደጅ መግቢያ ተቀመጡ። |
ነገር ግን በየኰረብቶች ላይ የነበሩትን የአሕዛብ መሠዊያዎችን አላስወገደም፤ ሕዝቡም መሥዋዕት ማቅረባቸውንና ዕጣን ማጠናቸውን እንደ ቀጠሉ ነበር፤ የቤተ መቅደሱን ሰሜናዊ ቅጽር በር ያሠራ ይኸው ኢዮአታም ነበር።
ኢዮአታም የቤተ መቅደሱን ሰሜናዊ በር እንደገና ሠራ፤ በተጨማሪም በኢየሩሳሌም በሚገኘው ዖፌል ተብሎ በሚጠራው ኰረብታማ ቦታ የከተማ ቅጽሮችን በመሥራት ብዙ ሥራ አከናውኖአል፤
ንጉሥ ኢዮአቄምና መኳንንቱ፥ እንዲሁም የጦር አዛዦቹ ኡሪያ የተናገረውን በሰሙ ጊዜ፥ ኡሪያ እንዲገደል ንጉሡ ፈለገ፤ ኡሪያ ግን ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ፈራ፤ ወደ ግብጽም ሸሽቶ አመለጠ፤
ሕዝቡና መሪዎቻቸው ሁሉ ባሪያዎቻቸውን ነጻ ለመልቀቅና እንደገና መልሰውም ባሪያዎች ላለማድረግ ተስማሙ፤ በዚህም ስምምነት መሠረት ሁሉንም ነጻ አወጡአቸው፤
የይሁዳና የኢየሩሳሌምን ታላላቅ ሰዎች፥ የቤተ መንግሥቱን ባለሥልጣኖች፥ ካህናቱንና ተቈርጦ በተከፈለው ጥጃ ብልቶች መካከል ያለፉትን የአገሪቱን ሕዝብ ሁሉ፥
ሕዝቡም ለማዳመጥ በሚችልበት ሁኔታ ባሮክ እኔ የነገርኩትን በብራና ጽፎት የነበረውን ቃል ሁሉ አነበበላቸው። በቤተ መቅደስ ውስጥ ይህን ያደረገው በጸሐፊው በሳፋን ልጅ በገማርያ ክፍል በኩል ዘልቆ ነበር፤ ክፍሉም የሚገኘው ወደ ቤተ መቅደስ ከሚያስገባው አዲስ የቅጽር በር አጠገብ በላይኛው አደባባይ በኩል አለፍ ብሎ ነበር።