በኢዮስያስ ዘመነ መንግሥት ነኮ የተባለው የግብጽ ንጉሥ የአሦርን ንጉሠ ነገሥት ለመርዳት ሠራዊቱን እየመራ ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ ተጓዘ፤ ንጉሥ ኢዮስያስም መጊዶ ላይ የግብጽን ሠራዊት ለማገድ ጦርነት ገጥሞ በዚያ ውጊያ ላይ ተገደለ፤
ኤርምያስ 22:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአባቱ ምትክ በይሁዳ ስለ ነገሠው ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ሻሉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ዳግመኛ ወደማይመለስበት ወደ ሩቅ አገር ይሄዳል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በአባቱ ምትክ በይሁዳ ላይ ስለ ነገሠው፣ ከዚህ ስፍራ በምርኮ ስለ ተወሰደው፣ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ሰሎ እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፤ “ከእንግዲህ አይመለስም፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአባቱ በኢዮስያስ ፋንታ ስለ ነገሠው ከዚህም ስፍራ ስለ ወጣው ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ሰሎም ጌታ እንዲህ ይላልና፦ “ዳግመኛ ወደዚህ አይመለስም፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአባቱ በኢዮስያስ ፋንታ ስለ ነገሠው፥ ከዚህም ስፍራ ስለ ወጣውና ስለማይመለሰው ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ፥ ስለ ሳሌም እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአባቱ በኢዮስያስ ፋንታ ስለ ነገሠው ከዚህም ስፍራ ስለ ወጣው ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ሰሎም እግዚአብሔር እንዲህ ይላልና፦ |
በኢዮስያስ ዘመነ መንግሥት ነኮ የተባለው የግብጽ ንጉሥ የአሦርን ንጉሠ ነገሥት ለመርዳት ሠራዊቱን እየመራ ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ ተጓዘ፤ ንጉሥ ኢዮስያስም መጊዶ ላይ የግብጽን ሠራዊት ለማገድ ጦርነት ገጥሞ በዚያ ውጊያ ላይ ተገደለ፤
ባለሟሎቹ የሆኑ ባለሥልጣኖችም ሬሳውን በሠረገላ ወደ ኢየሩሳሌም አምጥተው እዚያ በነገሥታት መካነ መቃብር ተቀበረ። የይሁዳም ሰዎችም የኢዮስያስን ልጅ ኢዮአካዝን መረጡ፤ ቀብተውም አነገሡት።
ኢዮአካዝ በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ኻያ ሦስት ዓመት ነበር፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ሦስት ወር ገዛ፤ እናቱም ሐሙጣል ተብላ የምትጠራ የልብና ከተማ ተወላጅ የሆነው የኤርምያስ ልጅ ነበረች፤
ንጉሥ ኒካዑ የኢዮስያስ ልጅ ኤልያቄም በአባቱ በኢዮስያስ እግር ተተክቶ በይሁዳ እንዲነግሥ አደረገ፤ ስሙንም በመለወጥ ኢዮአቄም ብሎ ጠራው፤ ኢዮአሐዝም በንጉሥ ነኮ ተማርኮ ወደ ግብጽ ተወሰደ፤ በዚያም ሞተ።
እንዲሁም የይሆሐናን ልጅ ዐዛርያስ፥ የመሺሌሞት ልጅ ቤሬክያ፥ የሻሉም ልጅ የይሒዝቂያና የሐድላይ ልጅ ዐማሣ የተባሉት አራት የታወቁ የኤፍሬም ግዛት መሪዎች የሠራዊቱን ድርጊት ተቃወሙ፤
ሒልቂያና የቀሩት ሰዎች ንጉሡ ባዘዛቸው መሠረት በኢየሩሳሌም ከተማ አዲሱ ክፍል ነዋሪ ወደሆነችው ሑልዳ ተብላ ወደምትጠራ ነቢይት ሄደው ስለ ተላኩበት ጉዳይ ጠየቁአት፤ የዚህች ነቢይት ባለቤት ሻሉም ተብሎ የሚጠራ የቲቅዋ ልጅ የሐርሐስ የልጅ ልጅ ሲሆን፥ እርሱም የቤተ መቅደሱ አልባሳት ኀላፊ ነበር፤ ሰዎቹም ለነቢይቱ ሁኔታውን በዝርዝር ገለጡላት፤
ሶፎንያስ የኩሺ ልጅ ሲሆን፥ ኩሺ የገዳልያ ልጅ፥ ገዳልያ የአማርያ ልጅ፥ አማርያ ደግሞ የንጉሥ ሕዝቅያስ ልጅ ነው፤ የአሞን ልጅ ኢዮስያስ የይሁዳ ንጉሥ በነበረበት ዘመን እግዚአብሔር ለሰፎንያስ የተናገረው ትንቢት እንደሚከተለው ነው።