ኤርምያስ 19:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጠላት ከተማይቱን ከቦ ሕዝቡን ለመጨረስ ያስጨንቋቸዋል፤ በዚህ ጊዜ ምግብ ሁሉ አልቆ ሕዝቡ ስለሚራብ እርስ በርሳቸው ይባላሉ፤ እንዲያውም ወላጆች የልጆቻቸውን ሥጋ ይበላሉ።’ ” አዲሱ መደበኛ ትርጒም የወንዶችና የሴቶች ልጆቻቸውን ሥጋ እንዲበሉ አደርጋለሁ፤ ሕይወታቸውን ለማጥፋት የሚሹ ጠላቶቻቸው ከብበው ሲያስጨንቋቸው፣ አንዱ የሌላውን ሥጋ ይበላል።’ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የወንዶችና የሴቶች ልጆቻቸውንም ሥጋ አበላቸዋለሁ፥ ጠላቶቻቸውንና ነፍሳቸውን የሚሹት በሚያስጨንቋቸው ጭንቀትና ከበባ ሁሉም የባልንጀሮቻቸውን ሥጋ ይበላሉ።’ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የወንዶችና የሴቶች ልጆቻቸውንም ሥጋ አበላቸዋለሁ፤ ሁሉም እያንዳንዳቸው ጠላቶቻቸውና ነፍሳቸውን የሚሹት በሚያስጨንቋቸው ጭንቀትና መከበብ የባልንጀሮቻቸውን ሥጋ ይበላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የወንዶችና የሴቶች ልጆቻቸውንም ሥጋ አበላቸዋለሁ፥ ሁሉም ጠላቶቻቸውንና ነፍሳቸውን የሚሹት በሚያስጨንቋቸው ጭንቀትና መከበብ የባልንጀሮቻቸውን ሥጋ ይበላሉ። |
በአንድ በኩል ሆዳቸው እስኪሞላ ይበላሉ፤ ነገር ግን እንደ ተራቡ ናቸው፤ እንዲሁም በሌላ በኩል አግበስብሰው ይውጣሉ፤ ነገር ግን አይጠግቡም፤ የልጆቻቸውን ሥጋ እንኳ እስከ መብላት ይደርሳሉ።
ያን ጊዜ አባቶችንና ልጆቻቸውን ሁሉንም እንደ ማድጋ እርስ በርሳቸው አጋጫቸዋለሁ፤ ምንም ዐይነት ሐዘኔታ፥ ርኅራኄ ወይም ምሕረት እነርሱን ከማጥፋት ሊያግደኝ አይችልም።”
“ንጉሥ ሆይ! እነዚህ ሰዎች ታላቅ በደል ፈጽመዋል፤ እነሆ ኤርምያስን ጒድጓድ ውስጥ ከተውታል፤ በከተማይቱ ምግብ ስለሌለ እዚያው በረሀብ መሞቱ ነው።”
ጌታ ሆይ! ተመልከት! ከአሁን ቀደም እንደዚህ የጨከንክበት ሕዝብ አለ ወይ? ሴቶች የወለዱአቸውንና ያሳደጓቸውን ሕፃናት ይብሉን! በጌታ ቤተ መቅደስ ውስጥስ ካህናትና ነቢያት ይገደሉን!
በዚህም ምክንያት በኢየሩሳሌም ያሉ ወላጆች በእርግጥ ልጆቻቸውን ይበላሉ፤ ልጆችም ወላጆቻቸውን ይበላሉ፤ በዚህ ዐይነት ሁላችሁንም እቀጣለሁ፤ የተረፉትንም በአራቱ ማእዘን እበትናቸዋለሁ።