ኤርምያስ 19:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር ቃሉን እንድናገርበት ካዘዘኝ ከቶፌት ተመልሼ መጣሁ፤ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አደባባይም ቆሜ እንዲህ ብዬ ነገርኳቸው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤርምያስም እግዚአብሔር ትንቢት እንዲናገር ልኮት ከነበረበት ከቶፌት ተመልሶ፣ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አደባባይ በመቆም፣ ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ አለ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤርምያስም ጌታ ትንቢት እንዲናገር ልኮት ከነበረበት ስፍራ ከቶፌት መጣ፥ በጌታም ቤት አደባባይ ቆሞ ለሕዝብ ሁሉ እንዲህ አለ፦ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤርምያስም እግዚአብሔር ትንቢት ሊናገር ወደዚያ ልኮት ከነበረው ስፍራ ከቶፌት ተመለሰ፤ በእግዚአብሔርም ቤት አደባባይ ቆሞ ለሕዝቡ ሁሉ እንዲህ አላቸው፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤርምያስም እግዚአብሔር ትንቢት ሊናገር ወደዚያ ልኮት ከነበረው ስፍራ ከቶፌት መጣ፥ በእግዚአብሔርም ቤት አደባባይ ቆሞ ለሕዝብ ሁሉ፦ |
እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፦ “የይሁዳ ንጉሥ ከከተማይቱ በሚወጣበትና በሚገባበት ወደ ሕዝቡ ቅጽር በር እንዲሁም በኢየሩሳሌም ወደሚገኙት ወደ ሌሎቹም ቅጽር በሮች ሄደህ ቁም፤