ኤርምያስ 18:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ አንድን ሕዝብ ወይም መንግሥት፥ ‘እነቅላለሁ ወይም ሰባብሬ አጠፋለሁ’ ብዬ በተናገርኩ ጊዜ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ሕዝብ ወይም መንግሥት እንዲነቀል፣ እንዲፈርስና እንዲጠፋ በተናገርሁ ጊዜ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሕዝብና በመንግሥት ላይ እንደምነቅል እንደማፈርስም እንደማጠፋም በተናገርሁ ጊዜ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አጠፋቸውና እደመስሳቸው ዘንድ በሕዝብ ላይና በመንግሥት ላይ ቍርጥ ነገርን ተናገርሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለ ሕዝብ ስለ መንግሥትም እነቅል አፈርስም አጠፋም ዘንድ በተናገርሁ ጊዜ፥ |
ምናልባት ሕዝቡ አዳምጠው ከክፉ መንገዳቸው ይመለሱ ይሆናል፤ የሚመለሱም ከሆነ ከክፋታቸው ሁሉ የተነሣ በእነርሱ ላይ ላመጣ ያቀድኩትን ጥፋት እተዋለሁ።”
እነርሱን ለመንቀልና ለማፍረስ፥ ለመገለባበጥና ለማጥፋት፥ ለመደምሰስም እከታተል የነበርኩትን ያኽል፥ እነርሱን እንደገና ለመትከልና ለማነጽም እከታተላለሁ።
‘በዚህች ምድር የምትኖሩ ቢሆን እኔ እንደገና አንጻችኋለሁ እንጂ አላፈርሳችሁም፤ እተክላችኋለሁ እንጂ አልነቅላችሁም፤ በእናንተ ላይ ያመጣሁት ጥፋት ታላቅ ሐዘን ሆኖብኛል፤
ነገር ግን ኀይሉ በገነነ ጊዜ መንግሥቱ ይፈርስና በአራት የዓለም ማእዘን ይከፈላል፤ በቦታውም የእርሱ ዘሮች ያልሆኑ ነገሥታት ይተካሉ፤ ይሁን እንጂ ከእነርሱ አንዱ እንኳ የእርሱን ያኽል ኀይል አይኖረውም፤ ይህም የሚሆነው ያ መንግሥት ፈርሶ እንደገና ለሌሎችም ስለሚከፋፈል ነው።
እኔ ጌታ እግዚአብሔር ወደ ኃጢአተኛው የእስራኤል መንግሥት እመለከታለሁ፤ እርስዋንም ከምድር ገጽ አጠፋለሁ፤ ሆኖም የያዕቆብን ዘር ሙሉ በሙሉ አልደመስስም። ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
እግዚአብሔር የነነዌ ሰዎች ያደረጉትንና ከክፉ መንገዳቸው መመለሳቸውን ተመለከተ፤ ስለዚህም ራርቶላቸው በእነርሱ ላይ ሊያመጣ የነበረውን ቅጣት አልፈጸመም።