ኤርምያስ 18:17 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ትቢያ በምሥራቅ ነፋስ እንደሚበተን፥ ሕዝቤን በጠላቶቻቸው ፊት እበትናቸዋለሁ። ፊቴን ከእነርሱ መልሼ ጀርባዬን እሰጣቸዋለሁ። ጥፋት በሚመጣባቸውም ጊዜ ፈጽሞ አልረዳቸውም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከምሥራቅ እንደሚወጣ ነፋስ፣ በጠላቶቻቸው ፊት እበትናቸዋለሁ፤ በመጥፊያቸው ቀን፣ ጀርባዬን እንጂ ፊቴን አላሳያቸውም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጠላት ፊት እንደ ምሥራቅ ነፋስ እበትናቸዋለሁ፥ በጥፋታቸውም ቀን ጀርባዬን እንጂ ፊቴን አላሳያቸውም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በጠላት ፊት እንደ በረሃ ዐውሎ ነፋስ እበትናቸዋለሁ፤ በጥፋታቸውም ቀን ጀርባዬን እንጂ ፊቴን አላሳያቸውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በጠላት ፊት እንደ ምሥራቅ ነፋስ እበትናቸዋለሁ፥ በጥፋታቸውም ቀን ጀርባዬን እንጂ ፊቴን አላሳያቸውም። |
ዛፍን ‘አባታችን’፥ አለትንም ‘የወለድሽን እናታችን’ የምትሉ ሁሉ ኀፍረት ይደርስባችኋል፤ ይህም የሚሆነው ወደ እኔ በመመለስ ፈንታ ከእኔ ስለ ራቃችሁ ነው፤ መከራ ሲደርስባችሁ ግን መጥቼ እንዳድናችሁ ትጠይቁኛላችሁ።
ቅጥረኞች ወታደሮችዋም እንደ ሰቡ ወይፈኖች ናቸው፤ ወደ ኋላ ተመልሰው ይሸሻሉ፤ የፍርድና የጥፋት ቀን ስለ ደረሰባቸው፥ ጸንተው መዋጋት አይችሉም።
በወንድሞቹ መካከል ፍሬያማ ቢሆንም የእግዚአብሔር ቅጣት የሆነው የምሥራቁ ነፋስ ከምድረ በዳ ተነሥቶ ይመጣል፤ ምንጩ ይቆማል፤ ወንዙም ይደርቃል። ነፋሱም የነበሩትን ውድ ዕቃዎች ሁሉ ገፎ ይወስድበታል።
“እግዚአብሔር ለጠላቶችህ በአንተ ላይ ድልን ይሰጣቸዋል፤ በአንድ በኩል ትመጣባቸዋለህ፤ ነገር ግን ከእነርሱ ለማምለጥ በሰባት አቅጣጫ ትሸሻለህ፤ በምድር ላይ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ በአንተ ላይ የሚደርሰውን ነገር በሚያዩበት ጊዜ በፍርሃት ይሸበራሉ፤
“እግዚአብሔር በመላው ዓለም በሕዝቦች መካከል ከአንድ የምድር ዳርቻ እስከ ሌላው ድረስ ይበትንሃል፤ በዚያም አንተም ሆንክ የቀድሞ አባቶችህ ሰግዳችሁላቸው የማታውቁትን ከእንጨትና ከድንጋይ የተሠሩትን ባዕዳን አማልክት ታመልካለህ።
ይህም በሚሆንበት ጊዜ እኔ በእነርሱ ላይ ተቈጥቼ እለያቸዋለሁ፤ ፊቴን ከእነርሱ እሰውራለሁ፤ እነርሱም ይደመሰሳሉ፤ በእነርሱም ላይ ብዙ አሠቃቂ መቅሠፍት ይመጣባቸዋል፤ በዚያን ጊዜ፥ ‘ይህ ችግር የመጣብን አምላካችን በመካከላችን ስለሌለ አይደለምን?’ ይላሉ።