ኤርምያስ 15:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “በእርግጥ ለመልካም ዓላማ እታደግሃለሁ፤ በችግርና በመከራ ጊዜ ጠላቶችህ አንተን እንዲለማመጡ አደርጋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፤ “በርግጥ ለበጎ ዐላማ እታደግሃለሁ፤ በመከራና በጭንቅ ጊዜም፣ ጠላቶችህ ደጅ እንዲጠኑህ በእውነት አደርጋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እንዲህ አለ፦ በእውነት ለመልካም ነገር አጸናሃለሁ፤ በእውነት በመከራና በጭንቅ ጊዜ ጠላትህ እንዲለምንህ አደርገዋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ! በመከራቸውና በጭንቃቸው ጊዜ በጠላቶቻቸው ዘንድ ስለ እነርሱ በጎ ነገር በአንተ ፊት የቆምሁ ባልሆን ይህ ለእነርሱ መከናወን ይሁን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ በእውነት ለደኅንነትህ አጸናሃለሁ፥ በእውነት በመከራና በጭንቅ ጊዜ ጠላትህ እንዲለምንህ አደርገዋለሁ። |
ይኸውም ኃጢአተኞች መቶ ጊዜ ወንጀል ቢሠሩም ለረጅም ዘመን ይኖራሉ፤ ይሁን እንጂ እግዚአብሔርን ለሚፈሩና ለሚያከብሩ ሁሉ ነገር እንደሚሰምርላቸው ዐውቃለሁ።
እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ! እኔ አምላክህ ነኝ፥ ተስፋ አትቊረጥ! እኔ አበረታሃለሁ፥ እረዳህማለሁ፤ ድል ነሺ በሆነ ክንዴ እደግፍሃለሁ።
“የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከነሠራዊቱ ከተማይቱን ለመውጋት በመክበብ ላይ ይገኛል፤ ስለዚህ ምናልባት በረድኤት ከእኛ ጋር ሆኖ ድንቅ ሥራውን በመግለጥ ናቡከደነፆርን እንዲመለስ ያደርግልን እንደ ሆነ እግዚአብሔርን ጠይቅልን።”
ዘግየት ብሎም ንጉሥ ሴዴቅያስ መልእክተኛ ልኮ አስወሰደኝና በቤተ መንግሥቱ በግል ሲያነጋግረኝ “ከእግዚአብሔር የተነገረህ የትንቢት ቃል አለን?” ብሎ ጠየቀኝ። “አዎ፥ አለ!” ብዬ ንግግሬን በመቀጠል “አንተ ለባቢሎን ንጉሥ ተላልፈህ ትሰጣለህ” አልኩት።
ንጉሥ ሴዴቅያስ የሼሌምያን ልጅ የሁካልንና የማዕያን ልጅ ካህኑን ሶፎንያስን ወደ እኔ ወደ ኤርምያስ ልኮ “ስለ ሕዝባችን ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ጸልይ” ብለው እንዲጠይቁኝ አደረገ።
ንጉሥ ሴዴቅያስ ልኮ ወደ እርሱ አስጠራኝና በቤተ መቅደሱ ሦስተኛ በር አጠገብ እንዲህ አለኝ፦ “እነሆ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ ነው፤ አንዳች ነገር ሳትደብቅ እንድትነግረኝ እፈልጋለሁ።”
“እባክህ የምንጠይቅህን ነገር አድርግልን! ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይልን! ከስደት ለተረፍነው ሁሉ ጸልይልን! ቀድሞ ብዙዎች ነበርን፤ አሁን ግን አንተ ራስህ እንደምታየን ጥቂቶች ብቻ ቀርተናል፤