ኤርምያስ 13:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ ሂድና መታጠቂያውን በአለት ንቃቃት ውስጥ ደብቀው።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ገዝተህ የታጠቅህበትን መቀነት ይዘህ ወደ ኤፍራጥስ ሂድ፤ በዚያም በዐለት ንቃቃት ውስጥ ሸሽገው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም አለኝ፦ “የገዛኸውን በወገብህ ያለውን መታጠቂያ ወስድ፥ ተነሣም፥ ወደ ኤፍራጥስም ሂድ፥ በዚያም በተሰነጠቀ ዓለት ውስጥ ሸሽጋት።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ለወገብህ የገዛሃትን ያቺን መታጠቂያ ወስደህ ተነሥ፤ ወደ ኤፍራጥስም ሂድ፤ በዚያም በተሰነጠቀ ዓለት ውስጥ ሸሽጋት።” |
የኢየሩሳሌም ሕዝብ ሆይ! ምጥ እንደ ያዛት ሴት እየቃተታችሁ ተንፈራፈሩ፤ ከከተማ ተባራችሁ በሜዳ ላይ ትሰፍራላችሁ ወደ ባቢሎንም ትሄዳላችሁ፤ ይሁን እንጂ በዚያ እግዚአብሔር ያድናችኋል፤ ከጠላቶቻችሁም እጅ ይታደጋችኋል።