ኢሳይያስ 60:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቄዳር የበግ መንጋዎች ሁሉ ወደ አንቺ ይሰበሰባሉ፤ የነባዮት አውራ በጎችም ለመሥዋዕትነት ያገለግሉሻል፤ በመሠዊያም ላይ ለመሥዋዕትነት ለመቅረብ ተቀባይነት ይኖራቸዋል። የተከበረውን ቤተ መቅደሴንም አስጌጣለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቄዳር የበግ መንጋ ሁሉ ወደ አንቺ ይሰበሰባል፤ የነባዮት አውራ በጎች ያገለግሉሻል። እነዚህም በመሠዊያዬ ላይ ተቀባይነት የሚኖራቸው መሥዋዕቶች ይሆናሉ፤ እኔም የክብር መቅደሴን ግርማ አጐናጽፈዋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቄዳር መንጎች ሁሉ ወደ አንቺ ይሰበሰባሉ የነባዮትም አውራ በጎች ያገለግሉሻል፤ እኔን ደስ ሊያሰኙ በመሠዊያዬ ላይ ይወጣሉ፥ የክብሬንም ቤት አከብራለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቄዳር በጎች ሁሉ ወደ አንቺ ይሰበሰባሉ፤ የነባዮትም አውራ በጎች ወደ አንቺ ይመጣሉ፤ በመሠዊያዬ ላይም የተመረጠው መሥዋዕት ይቀርባል፤ የጸሎቴ ቤትም ይከብራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቄዳር መንጎች ሁሉ ወደ አንቺ ይሰበሰባሉ የነባዮትም አውራ በጎች ያገለግሉሻል፥ እኔን ደስ ሊያሰኙ በመሠዊያዬ ላይ ይወጣሉ፥ የክብሬንም ቤት አከብራለሁ። |
ስለዚህ አሁን ሰባት ኰርማዎችንና ሰባት አውራ በጎችን ይዛችሁ ወደ አገልጋዬ ወደ ኢዮብ ሂዱ፤ እዚያም ስለ ራሳችሁ ኃጢአት የሚቃጠል መሥዋዕት አቅርቡ፤ አገልጋዬ ኢዮብ ይጸልይላችኋል፤ እኔም ጸሎቱን ሰምቼ በበደላችሁ መጠን አልቀጣችሁም፤ እናንተ እንደ ኢዮብ ስለ እኔ ትክክል የሆነውን ነገር አልተናገራችሁም።”
እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ! ስሙኝ፤ እኔ ጥቊር ነኝ፤ ይሁን እንጂ ውብ ነኝ፤ የመልኬ ጥቊረት እንደ ቄዳር ድንኳን ነው፤ ውበቴ ግን እንደ ሰሎሞን ቤተ መንግሥት መጋረጃዎች ነው።
በዚያን ጊዜ በግብጽ ምድር መካከል ለእግዚአብሔር መሠዊያ ይሠራል፤ እንዲሁም በግብጽ ጠረፍ ላይ ለእግዚአብሔር የተለየ የድንጋይ ዐምድ ይተከላል።
እግዚአብሔር ለግብጽ ሕዝብ ራሱን ይገልጥላቸዋል፤ በዚያን ጊዜ እነርሱም አምላክነቱን ዐውቀው ይሰግዱለታል፤ መሥዋዕትና መባም ያቀርቡለታል፤ ለእግዚአብሔርም ስእለት ይሳላሉ፤ ስእለታቸውንም ሁሉ ይፈጽማሉ።
ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “የሠራተኞች የሥራ ውል እንደሚያልቅ ልክ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የቄዳር ነገዶች ክብር ይወገዳል፤
በረሓና በበረሓ የሚገኙ ከተሞች፦ እንዲሁም የቄዳር ሕዝቦች የሚኖሩባት መንደር ድምፃቸውን ከፍ ያድርጉ፤ የሴላዕ ከተማ ነዋሪዎች በደስታ ይዘምሩ፤ ከተራሮችም ጫፍ የእልልታ ድምፅ ያሰሙ።
“እነርሱን ወደ ተቀደሰው ተራራዬ አምጥቼ በጸሎት ቤቴም ደስ እንዲላቸው አደርጋለሁ፤ በመሠዊያዬም ላይ የሚያቀርቡትን የሚቃጠልና ሌሎችን መሥዋዕቶች ሁሉ እቀበላለሁ፤ ይህንንም የማደርገው ቤቴ የሕዝቦች ሁሉ ጸሎት ቤት ተብሎ ስለሚጠራ ነው።”
ቤተ መቅደሴ ያረፈበትን ቦታ ለማስዋብ የሊባኖስ ግርማ የሆኑት ዝግባ አስታና ጥድ ወደ አንቺ እንዲመጡ ይደረጋሉ፤ እኔም የእግሬ ማረፊያ የሆነውን አከብረዋለሁ።
ነገር ግን እኔ ልዑል እግዚአብሔር በሀገሪቱ ውስጥ በቅዱሱ ተራራዬ ላይ እስራኤላውያን በሙሉ ያመልኩኛል እላለሁ፤ እዚያ እቀበላቸዋለሁ፤ እንዲሁም በዚያ ምርጥ መባዎችንና የተቀደሱ ዕቃዎች ስጦታዎችን ከእናንተ እጠባበቃለሁ።
የዘመኑ ፍጻሜ ሲደርስ፥ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የተሠራበት ተራራ ከሌሎች ተራራዎች ሁሉ በልጦ ይታያል፤ ከኰረብቶችም ሁሉ እጅግ ከፍ ይላል፤ የብዙ መንግሥታት ሕዝቦችም ወደ እርሱ ይጐርፋሉ።
እናንተን የሚነካ የእርሱን ዓይን ብሌን እንደሚነካ ሆኖ ይቈጠራል። የክብር ጌታ በበዘበዙአችሁ ሕዝቦች ላይ በላከኝ ጊዜ የተናገራቸው ቃላት እነዚህ ናቸው።
እንግዲህ ወንድሞቼ ሆይ! እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ፥ ሕያውና የተቀደሰ መሥዋዕት አድርጋችሁ ሁለንተናችሁን እንድታቀርቡ በመሐሪው በእግዚአብሔር ስም እለምናችኋለሁ፤ ይህም ማቅረብ የሚገባችሁ ቅንነት ያለው እውነተኛ የእግዚአብሔር አገልግሎት ነው።
ይህም ጸጋ የተሰጠኝ የእግዚአብሔርን የምሥራች ቃል ለአሕዛብ በማብሠር እንደ ካህን ሆኜ ኢየሱስ ክርስቶስን ለማገልገል ነው፤ ስለዚህ አሕዛብ በመንፈስ ቅዱስ የተቀደሰና እግዚአብሔርንም ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ አገለግላለሁ።