ኢሳይያስ 55:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለማይጠቅም ምግብ ገንዘባችሁን ለምን ታወጣላችሁ? ለማያጠግብ ነገር ጒልበታችሁን ለምን ታባክናላችሁ? አሁንም በጥንቃቄ አድምጡኝና መልካም የሆነውን ምግብ ብሉ፤ በምርጥ ምግብም ራሳችሁን አስደስቱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ገንዘባችሁን እንጀራ ባልሆነ ነገር ላይ ለምን ታጠፋላችሁ? በማያጠግብስ ነገር ላይ ለምን ጕልበታችሁን ትጨርሳላችሁ? ስሙ፤ እኔን ስሙኝ፤ መልካም የሆነውንም ብሉ፤ ነፍሳችሁም በጥሩ ምግብ ትደሰታለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንጀራ ላልሆነ ነገር ገንዘብን ለምን ታባክናላችሁ፥ የድካማችሁንም ዋጋ በማያጠግብ ነገር ለምን ትለውጣላችሁ? አድምጡኝ፥ በረከትንም ብሉ፥ ሰውነታችሁም በጮማ ደስ ይበለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ገንዘብን እንጀራ ላይደለ፥ የድካማችሁንም ዋጋ ለማያጠግብ ነገር ለምን ትመዝናላችሁ? አድምጡኝ፤ በረከትንም ብሉ፤ ሰውነታችሁም በበረከት ደስ ይበለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ገንዘብን እንጀራ ላይደለ፥ የድካማችሁንም ዋጋ ለማያጠግብ ነገር ለምን ትመዝናላችሁ? አድምጡኝ፥ በረከትንም ብሉ፥ ሰውነታችሁም በጮማ ደስ ይበለው። |
እንዲህም አላቸው፤ “በጥሞና ትእዛዞቼን ብታዳምጡና በፊቴ መልካም የሆነውን ነገር በታዛዥነት ብታደርጉ፥ ኅጎቼንም ሁሉ ብትጠበቁ፥ በግብጻውያን ላይ ካመጣሁባቸው በሽታዎች በአንዱ እንኳ አልቀጣችሁም፤ ፈዋሻችሁ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”
ፍላጻም ሆድ ዕቃውን እንደሚወጋው ዐይነት ሆነ፤ ወደ ወጥመድ እንደሚገባ ወፍ መሰለ፤ ይህ ሁሉ ሲሆን ሕይወቱ በአደጋ ላይ ለመውደቅ መቃረቡን አላወቀም።
እግዚአብሔር ለሰው ምድራዊ ሀብትንና ብልጽግናን ክብርንም ሁሉ ይሰጠዋል፤ ከሚያስፈልገውም ነገር ሁሉ ምንም አያጐድልበትም፤ ይሁን እንጂ በሚሰጠው ሀብት ሁሉ አይደሰትበትም፤ ይልቁንም እርሱ ደክሞ ያፈራውን ሌላ ሰው ይደሰትበታል። ይህም ከንቱና እጅግ የከፋ በደል ነው።
በዚያንም ጊዜ እናንተን ከአሦራውያን የጭቈና አገዛዝ ነጻ አወጣችኋለሁ፤ ከዚያን በኋላ የአገዛዝ ቀንበራቸው ከውፍረታችሁ የተነሣ ይሰበራል እንጂ በእናንተ ጫንቃ ላይ እንደተጫነ አይቀርም።”
የሠራዊት አምላክ በዚህች በጽዮን ተራራ ለዓለም ሕዝቦች ሁሉ ታላቅ ግብዣ ያዘጋጃል፤ በግብዣውም ላይ ምርጥ የወይን ጠጅና፥ የተሟላ ምግብ ይዘጋጃል።
ተቃጥሎ ዐመድ የሚሆነውን እንጨት እስከ ማምለክ ድረስ ሰው እንዴት ሞኝ ይሆናል? የሞኝነት አስተሳሰቡ አሳስቶታል፤ ራሱን ማዳን አይችልም፤ ወይም “ይህ በቀኝ እጄ ያለው ነገር ጣዖት እንጂ አምላክ አይደለም።” ብሎ መናገር አይችልም።
አንዳንድ ሰዎች ኰረጆአቸውን ከፍተው ወርቅ እንደ ልባቸው ይመዛሉ፤ ብሩንም በሚዛን ይመዝናሉ፤ ጣዖት አድርጎ እንዲሠራላቸውም አንጥረኛ ይቀጥራሉ፤ ከተሠራም በኋላ እየሰገዱ ያመልኩታል።
እግዚአብሔር በኃይሉና በሥልጣኑ እንዲህ ሲል ማለ፦ “ከእንግዲህ ወዲያ እህልሽን ጠላቶችሽ እንዲበሉት አላደርግም፤ የደከምሽበትን አዲስ የወይን ጠጅሽንም ባዕዳን እንዲጠጡት አላደርግም።
ነገር ግን በጐተራ የሰበሰቡትን እህል እነርሱ ራሳቸው በልተው እኔ እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ፤ የሰበሰቡትንም የወይን ዘለላ የወይን ጠጅ እነርሱ ራሳቸው በተቀደሰ አደባባዬ ይጠጡታል።
ሥራቸው ከንቱ አይሆንም፤ የወለዱአቸው ልጆችና የልጅ ልጆቻቸው በእግዚአብሔር የተባረኩ ስለሚሆኑ ልጆቹን የሚወልዱት ጥፋት እንዲደርስባቸው አይደለም።
“‘እንግዲህ የሚያዳምጡኝ ከሆኑ እነዚህ ሕዝብ ትእዛዜን እንዲጠብቁ ንገራቸው፤ በሰንበት ቀን ምንም ዐይነት ሸክም ይዘው በከተማይቱ በሮች አይግቡ፤ ሰንበትን የተቀደሰ ቀን አድርገው ያክብሩ እንጂ በዚያን ቀን ምንም ሥራ አይሥሩ።
ሕዝቤ ሁለት ኃጢአት ሠርተዋል፤ ይኸውም የሕይወት ውሃ ምንጭ የሆንኩትን እኔን ትተውኛል፤ ውሃ መቋጠር የማይችሉ የተሸነቈሩ ጒድጓዶችን ለራሳቸው ቆፍረዋል።”
“የእስራኤል ሕዝብ ነፋስን ለመጨበጥ በመሞከርና ቀኑን ሙሉ የምሥራቅ ነፋስን ሲያሳድዱ በመዋል ከንቱ ሆነዋል፤ ሐሰትንና ዐመፅን ያበዛሉ፤ ከአሦር ጋር ይዋዋላሉ፤ በሌላ በኩል ደግሞ የወይራ ዘይትን ወደ ግብጽ ይልካሉ።”
እነርሱ ነፋስን ዘርቶ ዐውሎ ነፋስን እንደሚያጭድ ይሆናሉ፤ ዛላ የሌለው የእህል አገዳ ምግብ ሊሆን አይችልም፤ ፍሬ ቢኖረውም እንኳ የሚበሉት ባዕዳን በሆኑ ነበር።
“ንጉሡ ሌሎች አገልጋዮችን እንደገና እንዲህ ሲል ላከ፤ ‘ወደ ተጠሩት ሰዎች ሂዱና፦ እነሆ፥ የሠርግ ድግሴን አዘጋጅቻለሁ፤ ሰንጋዎቼና የሰቡት ፍሪዳዎቼ ታርደዋል፤ ሁሉም ነገር ተዘጋጅቶአል፤ ስለዚህ ወደ ሠርጉ ግብዣ ኑ!’ ብላችሁ ንገሩአቸው።
ለሚጠፋ ምግብ አትሥሩ፤ ይልቅስ እግዚአብሔር አብ የማረጋገጫ ማኅተም ስለ አተመው የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ፥ የዘለዓለም ሕይወት ለሚሆነው ምግብ ሥሩ።”
ባልተለመደ በልዩ ልዩ ዐይነት ትምህርት አትማረኩ፤ ልባችን የመብል ሥነ ሥርዓቶችን በመጠበቅ ሳይሆን በጸጋ ቢጸና መልካም ነው፤ ይህን የምግብ ሥነ ሥርዓት የተከተሉ ሰዎች ምንም አልተጠቀሙም።