ኢሳይያስ 28:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነቢያቱና ካህናቱ እንኳ ሰክረው ይንገዳገዳሉ፤ ብዙ ወይን ጠጅና የሚያሰክርም ጠንካራ መጠጥ ስለ ጠጡ አእምሮአቸው ታውኮ ይሰናከላሉ፤ ነቢያቱ ሰክረው ከመደናበራቸው የተነሣ እግዚአብሔር የገለጠላቸውን ራእይ አያስተውሉም፤ ካህናቱም እጅግ ስለሚሰክሩ ለሚቀርብላቸው ጉዳይ ተገቢውን ውሳኔ መስጠት አይችሉም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህም በወይን ጠጅ ይንገዳገዳሉ፤ በሚያሰክርም መጠጥ ይወላገዳሉ፤ ካህናቱና ነቢያቱ በሚያሰክር መጠጥ ተንገዳገዱ፤ በወይን ጠጅ ነገር ተምታታባቸው፤ በሚያሰክር መጠጥ ተወላገዱ፤ ራእይ ሲያዩ ይስታሉ፤ ፍርድ ሲሰጡም ይሰናከላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህ ደግሞ ከወይን ጠጅ የተነሣ ይስታሉ፤ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ ይንገዳገዳሉ፤ ካህኑና ነቢዩ ከሚያሰክር መጠጥ የተነሣ ይስታሉ፥ በወይን ጠጅም ይቀባዥራሉ፥ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ ይንገዳገዳሉ፤ ራእይ ሲያዩ ይስታሉ፥ በፍርድም ይሰናከላሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚህም ደግሞ ከወይን ጠጅ የተነሣ ይስታሉ፤ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ አላዋቆች ይሆናሉ፤ ካህኑና ነቢዩ ከሚያሰክር መጠጥ የተነሣ ይስታሉ፤ በወይን ጠጅም ይዋጣሉ፤ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ ይበድላሉ፤ ይህም የዐይን ምትሐት ነው፤ በፍርድ ይሰናከላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚህ ደግሞ ከወይን ጠጅ የተነሣ ይስታሉ፥ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ ይፋንናሉ፥ ካህኑና ነቢዩ ከሚያሰክር መጠጥ የተነሣ ይስታሉ፥ በወይን ጠጅም ይዋጣሉ፥ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ ይፋንናሉ፥ በራእይ ይስታሉ፥ በፍርድም ይሰናከላሉ። |
በጨዋነት ያደገ ንጉሥና ለስካር ሳይሆን ብርታትና ኀይል ለማግኘት ብቻ በተወሰነ ጊዜ የሚበሉና የሚጠጡ መሪዎች ያሉአት አገር የተባረከች ናት።
የተዘበራረቀ ምክር እንዲሰጡ ያደረጋቸውም እግዚአብሔር ነው፤ በመጨረሻም ግብጽ በሁሉ ነገር በመሳሳት የገዛ ትፋቱ አዳልጦት እንደሚጥለው ሰካራም ትንገዳገዳለች።
እናንተ ግን ጥሪውን በመቀበል ፈንታ በዓል አደረጋችሁ፤ የምትበሉትንም በግና በሬ ዐረዳችሁ፤ ወይን ጠጅም ጠጥታችሁ “ነገ እንሞታለን ዛሬ እንብላ እንጠጣ!” አላችሁ።
የሰው ሁሉ ዕድል አንድ ዐይነት ይሆናል፤ ካህናትና ሕዝቡ፥ አገልጋዮችና አሳዳሪዎቻቸው፥ እመቤቲቱና አገልጋይቱ፥ ገዢዎችና ሻጮች፥ አበዳሪዎችና ተበዳሪዎች፥ ዕዳ ከፋይና ዕዳ አስከፋይ በአንድነት ይጠፋሉ።
ምድር እንደ ሰከረ ሰው ትንገዳገዳለች፤ በዐውሎ ነፋስ እንደ ተገፋ ጎጆም ትናወጣለች፤ እርስዋም የኃጢአትዋ ሸክም ስለሚጫናት ትወድቃለች፤ መነሣትም አትችልም።
ከለምለሙ ሸለቆ በላይ ላለችው የሰማርያ ከተማ ወዮላት! መሪዎችዋ በመጠጥ የተሞሉ ሰካራሞች ናቸው ነገር ግን እነርሱ ደርቆ እንደሚረግፍ አበባ ይሆናሉ።
የትንቢት ራእይ ሁሉ ትርጒም ከእናንተ ተሰውሮ እንደ ታሸገ መጽሐፍ ይሆናል፤ ወደሚያነብ ሰው ወስዳችሁ “አንብብልን” ብላችሁ ብትጠይቁት እንኳ “ስለ ታሸገ ላነበው አልችልም” ይላችኋል።
ገንዘብ አበዳሪዎች ሕዝቤን ያራቊታሉ፤ አራጣ አበዳሪዎችም ይበዘብዙአቸዋል፤ ሕዝቤ ሆይ፥ መሪዎቻችሁ ያስቱአችኋል፤ የምትሄዱበትንም መንገድ ያጣምማሉ።
እግዚአብሔር እንዲህ ሲል መለሰ፦ “ነቢያቱ በእኔ ስም ሐሰት ይናገራሉ፤ እኔ አላክኋቸውም፤ ትእዛዝም አልሰጠኋቸውም፤ አንድ ቃል እንኳ አልነገርኳቸውም፤ አየን የሚሉት ራእይ ሁሉ ከእኔ የተገኘ አይደለም፤ ትንቢታቸው ሁሉ የሐሰት ራእይ፥ መተት፥ ጣዖት አምልኮና ከሐሳባቸው ያፈለቁት ከንቱ ነገር ነው።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ለኢየሩሳሌም ሕዝብ እንዲህ ይላል፦ “ነቢያቱ የሚሉትን አትስሙ፤ እነርሱ በሐሰተኛ ተስፋ ይሞሉአችኋል፤ የሚነግሩአችሁም በሐሳባቸው ያለሙትን እንጂ እኔ የምነግራቸውን ቃል አይደለም፤
እንደ ጠላት ቀስቱን ገተረ፤ በቀኝ እጁ የያዘውን በእኛ ላይ አነጣጠረ፤ በኢየሩሳሌም ከተማ የምንመካባቸውን ሁሉ ገደለ፤ ቊጣውንም እንደ እሳት አቀጣጠለ።
አንተ ራስህ ጠጥተህ በመስከር ትንገዳገዳለህ፤ አንተም በተራህ በክብር ፈንታ ውርደትን ትለብሳለህ፤ እግዚአብሔር ኀይለኛ የቅጣት ጽዋ እንድትጠጣ ያደርግሃል፤ ክብርህን ወደ ውርደት ይለውጣል።
“ከነዚያ ከመከራ ቀኖች በኋላ ወዲያውኑ ፀሐይ ትጨልማለች፤ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፤ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፤ የሰማያት ኀይሎችም ይናወጣሉ።
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “በመብልና በመጠጥ ብዛት በስካርም በመባከንና ስለ ዓለማዊ ኑሮ በመጨነቅ ልባችሁ እንዳይዝል ተጠንቀቁ! አለበለዚያ ያ ቀን እንደ ወጥመድ በድንገት ይይዛችኋል።