ኢሳይያስ 21:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ራሴን ያዞረኛል፤ ከፍርሃት የተነሣም እንቀጠቀጣለሁ፤ ቀኑ ቶሎ እንዲመሽልኝ ተመኘሁ፤ ተስፋ ያደረግኹት ጭላንጭል አስደንጋጭ ሆነብኝ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልቤ ተናወጠ፤ ፍርሀት አንቀጠቀጠኝ፤ የጓጓሁለት ውጋጋን፣ ታላቅ ፍርሀት አሳደረብኝ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልቤ ራደ፥ ድንጋጤ አስደመመኝ፥ ተስፋ ያደረግሁትም ድንግዝግዝታ ፍርሃት አሳደረብኝ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልቤ ሳተ፤ ኀጢአቴም አሰጠመኝ፤ ሰውነቴም ደነገጠብኝ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልቤ ተንበደበደ፥ ድንጋጤ አስፈራኝ፥ ተስፋ ያደረግሁትም ድንግዝግዝታ መንቀጥቀጥ ሆነብኝ። |
ሃማን ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፦ “ከዚህም ሁሉ በላይ ንግሥት አስቴር ባዘጋጀችው ግብዣ ላይ ከንጉሡና ከእኔ በቀር ማንንም አልጠራችም፤ ለነገ በምታዘጋጀው ግብዣም ላይ እንደገና ተጠርተናል፤
ወይ ሥቃይ! ይህን ሁሉ ሥቃይ እንዴት መታገሥ እችላለሁ! ወይ ልቤ! የልቤ አመታት እንዴት ፈጠነ? የጥሩምባ ድምፅና የጦርነት ድምፅ እየሰማሁ፥ ዝም ብዬ መታገሥ አልችልም።
ሞቅ ባላቸው ጊዜ የመጠጥ ግብዣ አደርግላቸዋለሁ፤ እስኪሰክሩ ድረስም አጠጣቸዋለሁ፤ ከዚያም ዘለዓለማዊ እንቅልፍ ያንቀላፋሉ፤ እስከ መቼም አይነቁም።
መሳፍንትዋ፥ የጥበብ ሰዎችዋ፥ መሪዎችዋ፥ የጦር አዛዦችዋና ወታደሮችዋ ጠጥተው እንዲሰክሩ አደርጋለሁ፤ ከዚያም በኋላ ይተኛሉ፤ እስከ ዘለዓለም አይነቁም፤ ይህን የተናገርኩ እኔ ንጉሡ ነኝ፤ ስሜም የሠራዊት አምላክ ነው።
የሰው እጅ ጣቶች በድንገት ታይተው በቤተ መቅደሱ መቅረዝ ፊት ለፊት ባለው በተለሰነው የቤተ መንግሥቱ ግድግዳ ላይ መጻፍ ጀመሩ፤ እነዚያም ጣቶች በሚጽፉበት ጊዜ ንጉሡ አየ።