Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዳንኤል 5:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 ከዕለታት አንድ ቀን ንጉሥ ብልጣሶር በሺህ ለሚቈጠሩ መኳንንት ታላቅ ግብዣ አደረገ፤ ከእነርሱ ጋር የወይን ጠጅ እየጠጣ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ንጉሥ ቤልሻዛር ለሺሕ መኳንንቱ ታላቅ ግብዣ አደረገ፤ በሺሑም ፊት የወይን ጠጅ ይጠጣ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ንጉሡ ብልጣሶር ለሺህ መኳንንቶቹ ትልቅ ግብዣ አደረገ፥ በሺሁም ፊት የወይን ጠጅ ይጠጣ ነበር።

Ver Capítulo Copiar




ዳንኤል 5:1
11 Referencias Cruzadas  

በሦስተኛው ቀን የፈርዖን ልደት በዓል ስለ ነበረ ለመኳንንቱ ሁሉ ግብዣ አደረገ፤ በዚያኑ ቀን የወይን ጠጅ አሳላፊውና የእንጀራ ቤት ኀላፊው ከእስር ቤት ወጥተው በመኳንንቱ ፊት እንዲቀርቡ አደረገ።


አርጤክስስ በነገሠ በሦስተኛው ዓመት ባለሟሎቹ ለሆኑት ባለሥልጣኖችና አስተዳዳሪዎች ሁሉ ታላቅ ግብዣ አደረገ፤ በግብዣውም ላይ የፋርስና የሜዶን ጦር አዛዦች፥ አገረ ገዢዎችና የክፍላተ ሀገር አስተዳዳሪዎች ተገኝተው ነበር።


በዚያን ጊዜ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ጠጒራችሁን ተላጭታችሁ፥ ማቅም ለብሳችሁ እንድታዝኑና እንድታለቅሱ ጠርቶአችሁ ነበር፤


የሠራዊት አምላክ እንዲህ ብሎ ነግሮኛል፦ “በሕይወት እስካሉ ድረስ ይህ ክፉ በደል አይሰረይላቸውም፤ እኔ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”


እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በባቢሎን፥ በሕዝቦችዋ፥ በመሪዎችዋና በጥበበኞችዋ ላይ ሰይፍ ይመዘዝ!


ሞቅ ባላቸው ጊዜ የመጠጥ ግብዣ አደርግላቸዋለሁ፤ እስኪሰክሩ ድረስም አጠጣቸዋለሁ፤ ከዚያም ዘለዓለማዊ እንቅልፍ ያንቀላፋሉ፤ እስከ መቼም አይነቁም።


መሳፍንትዋ፥ የጥበብ ሰዎችዋ፥ መሪዎችዋ፥ የጦር አዛዦችዋና ወታደሮችዋ ጠጥተው እንዲሰክሩ አደርጋለሁ፤ ከዚያም በኋላ ይተኛሉ፤ እስከ ዘለዓለም አይነቁም፤ ይህን የተናገርኩ እኔ ንጉሡ ነኝ፤ ስሜም የሠራዊት አምላክ ነው።


በዚያኑ ሌሊት የባቢሎን ንጉሥ ብልጣሶር ተገደለ፤


እናንተ ሰካራሞች! እርስ በርሱ የተያያዘ እሾኽና ድርቆሽ በእሳት ተቃጥሎ እንደሚጠፋ፥ እናንተም እንዲሁ ትጠፋላችሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos