ኢሳይያስ 20:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ጊዜ በባሕር ዳርቻ የሚኖሩ ሰዎች፦ ‘እኛን ከአሦር ንጉሠ ነገሥት ያድኑናል ብለን ተስፋ ያደረግንባቸውና ወደ እነርሱ የተጠጋንባቸው አገሮች ምን እንደ ደረሰባቸው ተመልከቱ! እኛማ እንዴት እናመልጣለን?’ ” ይላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ቀን በዚህ ባሕር ዳርቻ የሚኖረው ሕዝብ፣ ‘የተመካንባቸው፣ ከአሦር ንጉሥ ለማምለጥና ነጻ ለመውጣት የተሸሸግንባቸው ምን እንደ ደረሰባቸው ተመልከቱ! እንግዲህ እኛስ እንዴት እናመልጣለን?’ ይላል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ቀን በዚች ባሕር ዳርቻ የሚቀመጡ፥ ‘እነሆ፥ ከአሦር ንጉሥ እንድን ዘንድ ለእርዳታ ወደ እነርሱ የሸሸንበት ተስፋችን ይህ ነበረ፤ እኛስ እንዴት እናመልጣለን?’ ይላሉ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን በዚች ደሴት የሚቀመጡ፦ እነሆ፥ ለርዳታ ወደ እነርሱ የሸሸንበት ተስፋችን ይህ ነበረ፤ ከአሦር ንጉሥ ራሳቸውን ያላዳኑ እኛን እንዴት ያድኑናል?” ይላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን በዚች ባሕር ዳርቻ የሚቀመጡ፦ እነሆ፥ ከአሦር ንጉሥ እንድን ዘንድ ለእርዳታ ወደ እነርሱ የሸሸንበት ተስፋችን ይህ ነበረ፥ እኛስ እንዴት እናመልጣለን? ይላሉ። |
በዚህ ሁሉ የግፍ ሥራችሁ እግዚአብሔር እናንተን በሚቀጣበት ጊዜ ምን ታደርጉ ይሆን? በእናንተ ላይ የሚደርሰውን ጥፋት ከሩቅ አገር በሚያመጣበት ጊዜስ ምን ይበጃችሁ ይሆን? ርዳታስ ለማግኘት የምትሄዱት ወደማን ነው? ሀብታችሁንስ የት ትሸሽጉታላችሁ?
የመሠረቱ መለኪያ ፍትሕ፥ ቱምቢውም ታማኝነት ይሆናሉ፤” መጠጊያችን ነው ብላችሁ የምትተማመኑበትን ሐሰት የበረዶ ወጀብ ይመታዋል፤ የምትሸሸጉበትንም ቦታ ጐርፍ ይጠራርገዋል።
ያ ቀን ምንኛ አስጨናቂ ይሆናል! እርሱን የመሰለ ቀን የለም፤ ለያዕቆብ ልጆች ለእስራኤላውያን የመከራ ዘመን ይሆናል፤ ሆኖም እነርሱ ከዚያ ሁሉ ጭንቀት ይድናሉ።”
ለጥፋት የተዳረግሽ ኢየሩሳሌም ሆይ! ወዮልሽ! ቀይ ልብስ የለበስሽበት ምክንያት ምንድን ነው? ጌጣጌጥ ማድረግሽና ዐይንሽንስ መኳልሽ ለምንድነው? ውሽሞችሽ ጠልተውሽ ሊገድሉሽ ስለሚፈልጉ ውበትሽን የምትንከባከቢው በከንቱ ነው።
ፍልስጥኤም የምትጠፋበት ጊዜ ደርሶአል፤ ከሞት ተርፈው ጢሮስንና ሲዶናን የሚረዱት ሁሉ ተቈራርጠው የሚቀሩበት ጊዜ ተቃርቦአል። እኔ እግዚአብሔር፥ ከሞት ተርፈው በባሕር ዳርቻ የምትገኘው የካፍቶር ዘሮች የሆኑትን ፍልስጥኤማውያን በሙሉ እደመስሳለሁ።
ሰዎች “ሁሉ ነገር ሰላምና የተረጋጋ ነው” ሲሉ እርጉዝ ሴትን ምጥ እንደሚይዛት ዐይነት ጥፋት በድንገት ይመጣባቸዋል፤ በምንም ዐይነት አያመልጡም።
ታዲያ፥ እኛ ይህን ታላቅ መዳን ችላ የምንል ከሆንን እንዴት እናመልጣለን? ይህን መዳን በመጀመሪያ ያበሠረው ጌታ ራሱ ነው፤ ከእርሱ የሰሙትም ሰዎች ይህንኑ አረጋግጠውልናል።