ኢሳይያስ 2:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ በብዙ መንግሥታት መካከል በመፍረድ አለመግባባትን ያስወግዳል፤ ስለዚህም ሰይፋቸውን ወደ ማረሻ፥ ጦራቸውንም ወደ ማጭድ ይለውጣሉ፤ መንግሥት በመንግሥት ላይ ጦርነት አያነሣም፤ ከዚያም በኋላ የጦር ትምህርት የሚማር አይኖርም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱ በሕዝቦች መካከል ይፈርዳል፤ የብዙ ሰዎችን አለመግባባት ያስወግዳል። እነርሱም ሰይፋቸውን ቀጥቅጠው ማረሻ፣ ጦራቸውንም ማጭድ ያደርጋሉ። ሕዝብ በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም፤ ጦርነትንም ከእንግዲህ አይማሩም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ በሕዝቦች መካከል ይፈርዳል፤ የብዙ ሰዎችን አለመግባባት ያስወግዳል። እነርሱም ሰይፋቸውን ቀጥቅጠው ማረሻ ጦራቸውንም ማጭድ ያደርጋሉ። ሕዝብ በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም፤ ጦርነትንም ከእንግዲህ አይማሩም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአሕዛብም መካከል ይፈርዳል፤ ብዙ አሕዛብንም ይዘልፋቸዋል፤ ሰይፋቸውንም ማረሻ፥ ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ፤ ሕዝብም በሕዝብ ላይ ሰይፍን አያነሣም፤ ሰልፍንም ከእንግዲህ ወዲህ አይማሩም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአሕዛብም መካከል ይፈርዳል፥ በብዙ አሕዛብም ላይ ይበይናል፥ ሰይፋቸውንም ማረሻ ጦራቸውንም ማጭድ ለማድረግ ይቀጠቅጣሉ፥ ሕዝብም በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሳም፥ ሰልፍም ከእንግዲህ ወዲህ አይማሩም። |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔ የምደግፈው የመረጥኩትና በእርሱም ደስ የሚለኝ አገልጋዬ ይህ ነው፤ መንፈሴ በእርሱ እንዲያድርበት አደርጋለሁ፤ እርሱ ለሕዝቦች ሁሉ ትክክለኛ ፍርድን ያመጣል።
ለንጉሣዊ ሥልጣኑ ወሰን የለውም፤ መንግሥቱም ዘለዓለማዊ ሰላም የሰፈነበት ይሆናል፤ ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘለዓለም፥ እውነትና ፍትሕ የሰፈነበት መንግሥት በዳዊት ዙፋን ላይ ተመሥርቶ እንዲጸና ያደርገዋል፤ የሠራዊት አምላክ ቅናት ይህን ለማድረግ ወስኖአል።
በዚያን ጊዜ ስለ እናንተ ከአራዊት፥ ከሰማይ ወፎችና በደረታቸው በምድር ላይ ከሚሳቡ ፍጥረቶች ጋር ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ ከምድሪቱም ላይ ቀስትን፥ ሰይፍንና ጦርነትን አስወግዳለሁ፤ እናንተንም በሰላም እንድታርፉ አደርጋለሁ።
እርሱ በብዙ ሕዝቦች መካከል ይፈርዳል፤ በቅርብና በሩቅ ባሉ ታላላቅ መንግሥታት መካከል ያለውን አለመግባባት ያስወግዳል፤ ስለ ሆነም ሰይፋቸውን ወደ ማረሻ፥ ጦራቸውንም ወደ ማጭድ ይለውጣሉ፤ መንግሥት በመንግሥት ላይ ጦርነት አያነሣም፤ ከዚያ በኋላም የጦር ትምህርት የሚማር አይኖርም።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እኔ ሠረገሎችን ከእስራኤል፥ የጦር ፈረሶችንም ከኢየሩሳሌም አስወግዳለሁ፤ የጦር ቀስቶችን እሰባብራለሁ፤ ንጉሥሽ በሕዝቦች መካከል ሰላም እንዲኖር ያደርጋል፤ ግዛቱም ከባሕር እስከ ባሕርና ከታላቁ ወንዝ ጀምሮ እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ይሆናል።”
እርሱ በመረጠው ሰው አማካይነት በዓለም ሁሉ ላይ በእውነት የሚፈርድበትን ቀን ወስኖአል፤ ይህንንም ለሁሉም ያረጋገጠው ያን የመረጠውን ሰው ከሞት በማስነሣቱ ነው።”
ከዚህ በኋላ ሰማይ ተከፍቶ አየሁ፤ እነሆ፥ ነጭ ፈረስም አየሁ፤ በፈረሱ ላይ የተቀመጠው ታማኝና እውነተኛ የሚባል ነው፤ እርሱ በትክክል ይፈርዳል፤ ይዋጋልም፤
እግዚአብሔርን የሚቃወሙ ይደመሰሳሉ፤ ከሰማይም ያንጐደጒድባቸዋል፤ እግዚአብሔር በዓለም ሁሉ ይፈርዳል፤ ለንጉሥም ኀይልን ይሰጠዋል፤ ለመረጠውም ክብሩን ከፍ ከፍ ያደርግለታል።”