ኢሳይያስ 1:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ፥ የእስራኤል ኀይል የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “በጠላቶቼ ላይ ኀይለኛ ቊጣዬን አውርጄ ተቃዋሚዎቼን እበቀላለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ጌታ፣ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፣ የእስራኤል ኀያል እንዲህ ይላል፤ “ወዮ! በባላንጣዎቼ ላይ ቍጣዬን እገልጣለሁ፤ ጠላቶቼንም እበቀላለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ጌታ፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ የእስራኤል ኀያል እንዲህ ይላል፤ “በባላንጣዎቼ ላይ ቁጣዬን እገልጣለሁ፤ ጠላቶቼንም እበቀላለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ለእስራኤል ኀያላን ወዮላቸው! በጠላቶች ላይ ቍጣዬ አይበርድም፤ ጠላቶችንም እበቀላለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ የእስራኤል ኃያል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ በጠላቶቼ ላይ ቍጣዬን እፈጽማለሁ፥ የሚቋቋሙኝንም እበቀላለሁ። |
እናንተ ግን ደስ ይላችኋል፤ በተቀደሰ በዓል ምሽት እንደምትዘምሩት ትዘምራላችሁ፤ የእስራኤል አምባ ወደ ሆነው ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሲሄዱ ዋሽንት እየነፉ እንደሚዘምሩት ሰዎች ትደሰታላችሁ።
ፈሪ ልብ ላላቸው “እነሆ አምላካችሁ ጠላቶቻችሁን ለመበቀልና የበደላቸውንም ዋጋ ለመክፈል መጥቶ ስለሚያድናችሁ በርቱ! አትፍሩ!” በሉአቸው።
ጨቋኞችሽ የገዛ ሥጋቸውን እንዲበሉ አደርጋለሁ፤ በወይን ጠጅ እንደሚሰክሩ የገዛ ደማቸውን ጠጥተው እንዲሰክሩ አደርጋለሁ። ከዚህም የተነሣ እኔ እግዚአብሔር አዳኝሽና ታዳጊሽ የእስራኤል ኀያል አምላክ መሆኔን የዓለም ሕዝብ ሁሉ ያውቃል።”
ልጆች የእናታቸውን ጡት እንደሚጠቡ የአንቺም ልጆች የሕዝቦችንና የነገሥታትን ሀብት በመውሰድ ይጠቀሙበታል፤ አንቺም እኔ እግዚአብሔር አዳኝሽና ታዳጊሽ ኀያሉ የያዕቆብ አምላክ መሆኔን ታውቂአለሽ።
ነገር ግን ታዳጊያቸው ብርቱ ነው፤ ስሙም የሠራዊት አምላክ ነው፤ እርሱ ራሱ ይረዳቸዋል፤ ሰላምን በምድር ላይ ያወርድላቸዋል፤ በባቢሎን ሕዝብ ላይ ገና መከራን ያመጣባቸዋል።”
ከሕዝባችሁ አንድ ሦስተኛው እጅ በራብና በበሽታ ያልቃል፤ አንድ ሦስተኛው ከከተማው ውጪ በሰይፍ ይገደላል፤ ሌላው ሦስተኛ እጅ በአራቱ ማእዘን በነፋስ እንዲበተን አድርጌ በኋላ በሰይፍ አሳድደዋለሁ።
“ቊጣዬ በእርሱ ላይ ይፈጸማል ኀይለኛ ቊጣዬንም በእነርሱ ላይ አውርጄ እረካለሁ ይህንንም ቊጣዬን በእነርሱ ላይ ባወረድኩ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር በቅናቴ የተናገርኩ መሆኔን ያውቃሉ።
እግዚአብሔር እናንተን ለማበልጸግና ቊጥራችሁንም ለማብዛት እንደ ወደደው ሁሉ እንደገናም እናንተን በማጥፋትና በመደምሰስ ደስ ይለዋል። ከዚህች ከምትወርሱአት ምድር ተነቃቅላችሁ ትጠፋላችሁ።
“ሕዝቦች ሆይ፥ እግዚአብሔር የአገልጋዮቹን ደም ይበቀላል፤ ጠላቶቹንም ይበቀላቸዋል፤ የሚጠሉትን ቀጥቶ የሕዝቡን ኃጢአት ያስተሰርያል፤ የምድሪቱን ርኲሰት ያነጻል ስለዚህ ከእርሱ ሕዝብ ጋር ደስ ይበላችሁ።”
ስለዚህ መቅሠፍቶችዋ ሁሉ በአንድ ቀን ይደርሱባታል፤ ሞትና ሐዘን ራብም ይደርሱባታል፤ በእሳትም ትቃጠላለች፤ በእርስዋ ላይ የሚፈርድባት ጌታ አምላክ ብርቱ ነው።”