ሆሴዕ 7:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሤራ ለመጐንጐን ልባቸው እንደ ምድጃ የጋለ ነው፤ ቊጣቸው ሌሊቱን ሙሉ ሲጤስ ያድራል፤ ሲነጋ ግን እንደሚነድ እሳት ይንበለበላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልባቸው እንደ ምድጃ የጋለ ነው፤ በተንኰል ይቀርቡታል፤ ቍጣቸው ሌሊቱን ሙሉ ይጤሳል፤ እንደሚነድድም እሳት በማለዳ ይንበለበላል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሴራቸው ልባቸው እንደ ምድጃ ተቃጥላለችና፤ ጋጋሪያቸው ሌሊቱን ሁሉ አንቀላፋ፤ በነጋም ጊዜ እንደ እሳት ነበልባል ነደደ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እያደቡ ልባቸውን እንደ ምድጃ አዘጋጅተዋል፤ ጋጋሪያቸውም ሌሊቱን ሁሉ አንቀላፋ፤ በጠባም ጊዜ እንደ እሳት ነበልባል ይነድዳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እያደቡ ልባቸውን እንደ ምድጃ አዘጋጅተዋል፥ አበዛቸውም ሌሊቱን ሁሉ አንቀላፋ፥ በጠባም ጊዜ እንደ እሳት ነበልባል ይነድዳል። |
“ሁሉም በቊጣ እንደ ምድጃ ግለው ገዢዎቻቸውን ፈጁ፤ ንጉሦቻቸውንም በየተራ አጠፉ፤ ይህም ሁሉ ሲሆን ከእነርሱ አንድ እንኳ የእኔን ርዳታ የጠየቀ የለም።”
ክፉ ሥራ ለመሥራት ለሚያቅዱና በመኝታቸው ሳሉ ተንኰል ለሚያውጠነጥኑ ወዮላቸው! ያን ለማድረግ ሥልጣን ስላላቸው ሌሊቱ ሲነጋ ዕቅዳቸውን በሥራ ላይ ያውሉታል።