እንዲህ ሲል ጸለየ፥ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ኪሩቤል ተብለው በሚጠሩ መላእክት ላይ የተቀመጥህ አንተ ብቻ አምላክ ነህ፤ የዓለምንም መንግሥታት የምትመራ አንተ ነህ፤ ሰማይንና ምድርን የፈጠርህ አንተ ነህ፤
ዕብራውያን 9:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በታቦትዋም ላይ ያለውን የኃጢአት ማስተስረያ መክደኛ በክንፋቸው የሚጋርዱ የክብር ኪሩቤል ነበሩ፤ ነገር ግን ስለ እነዚህ ነገሮች ሁሉ አሁን በዝርዝር መናገር አንችልም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በታቦቱም ላይ የስርየት መክደኛውን የሚጋርዱ የክብር ኪሩቤል ነበሩ፤ አሁን ግን ስለ እነዚህ ነገሮች በዝርዝር መናገር አንችልም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በላይዋም ማስተስሪያውን የሚጋርዱ የክብር ኪሩቤል ነበር፤ ስለ እነዚህም በዝርዝር የመናገሪያው ሰዓት አሁን አይደለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በላይዋም ማስተስረያውን የሚጋርዱ የክብር ኪሩቤል ነበሩ፤ ነገር ግን በየመልኩ እናገረው ዘንድ ዛሬ ጊዜው አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በላይዋም ማስተስሪያውን የሚጋርዱ የክብር ኪሩቤል ነበሩ፤ ስለ እነዚህም ስለ እያንዳንዳቸው ልንናገር አሁን አንችልም። |
እንዲህ ሲል ጸለየ፥ “የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ኪሩቤል ተብለው በሚጠሩ መላእክት ላይ የተቀመጥህ አንተ ብቻ አምላክ ነህ፤ የዓለምንም መንግሥታት የምትመራ አንተ ነህ፤ ሰማይንና ምድርን የፈጠርህ አንተ ነህ፤
ዳዊት ለልጁ ለሰሎሞን የቤተ መቅደሱን የዕቃ ግምጃ ቤቶቹን፥ በደርቡና በምድር ቤቱ የሚገኙትን ክፍሎችና ኃጢአት የሚሰረይበትን የቅድስተ ቅዱሳኑን አሠራር የሚገልጥ ዕቅድ ሰጠው።
የእስራኤል እረኛ፥ የዮሴፍን ልጆች እንደ መንጋ የምትመራ አምላክ ሆይ! በኪሩቤል ላይ ባለው ዙፋንህ ተቀምጠህ፥ ጸሎታችንን አድምጥ፤ ብርሃንህም ይብራ።
“እኔ በታቦቱ ስርየት መክደኛ በደመና የምገለጥበት ስለ ሆነ፥ መጋረጃውን አልፎ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን መግባት ያለበት ሁልጊዜ ሳይሆን፥ በአንድ በተወሰነ ቀን ብቻ መሆኑን፥ ለወንድምህ ለአሮን ንገረው፤ ይህን ትእዛዝ የማይፈጽም ከሆነ ይሞታል፤
ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር ለመነጋገር ወደ መገናኛው ድንኳን በገባ ጊዜ፥ እግዚአብሔር በኪሩቤል መካከል ካለው ከቃል ኪዳኑ ታቦት መክደኛ በላይ ሆኖ ሲናገረው ሰማ።
እነርሱ እስራኤላውያን ናቸው፤ እግዚአብሔርም እነርሱን ልጆቹ አደረጋቸው፤ ክብሩን ገለጠላቸው፤ ቃል ኪዳን ገባላቸው፤ ሕግን ሰጣቸው፤ እውነተኛውን የአምልኮ ሥርዓት አሳያቸው፤ የተስፋውንም ቃል ሰጣቸው።
ይህም የሆነው በአሁኑ ዘመን በቤተ ክርስቲያን አማካይነት በሰማይ ያሉት አለቆችና ባለሥልጣኖች የእግዚአብሔርን ጥበብ በየመልኩ እንዲያውቁ ነው።
እንግዲህ ምሕረት እንድንቀበልና ርዳታ በሚያስፈልገን ጊዜ ጸጋ እንድናገኝ ጸጋው ወደሚገኝበት ወደ እግዚአብሔር ዙፋን ያለ አንዳች ፍርሀት እንቅረብ።
እነዚህ ነቢያት ያገለግሉ የነበሩት እናንተን እንጂ ራሳቸውን እንዳልነበረ ተገልጦላቸዋል፤ ያገለገሉአችሁም ከሰማይ በተላከው በመንፈስ ቅዱስ አማካይነት አሁን ወንጌልን ያበሠሩአችሁ ሰዎች የነገሩአችሁን በመግለጥ ነው፤ ይህን ነገር መላእክት እንኳ ለማየት ይመኙት ነበር።
ስለዚህም ወደ ሴሎ መልእክተኞች ልከው በታቦቱ ላይ ባሉ ኪሩቤል ዙፋኑን ያደረገ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ግርማውን የሚገልጥበትን የቃል ኪዳኑን ታቦት አስመጡ፤ ሁለቱ የዔሊ ልጆች ሖፍኒና ፊንሐስም የቃል ኪዳኑን ታቦት አጅበው መጡ።