ጽዋዎች፥ የዐመድ ማጠራቀሚያዎች፥ ጐድጓዳ ሳሕኖች፥ የዕጣን ማቅረቢያ ዕቃዎች፥ ማንደጃዎች፥ ለቅድስተ ቅዱሳን በሮችና ለቤተ መቅደሱ ውጫዊ በሮች የሚያገለግሉ ማጠፊያዎች ነበሩ። እነዚህ ሁሉ ዕቃዎች ከወርቅ የተሠሩ ናቸው።
ዕብራውያን 9:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚህችኛዋ ክፍል ውስጥ የወርቅ ማዕጠንትና በወርቅ የተለበጠች የኪዳን ታቦት ነበሩባት፤ ከዚህችም የኪዳን ታቦት ውስጥ መና ያለባት የወርቅ መሶብ፥ ለምልማ የነበረችው የአሮን በትር፥ ዐሥሩ ትእዛዞች የተጻፉባት ጽላት ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያም ውስጥ የወርቅ ማዕጠንትና በወርቅ የተለበጠው የኪዳኑ ታቦት ነበሩ፤ ይህም ታቦት መና ያለበትን የወርቅ መሶብ፣ የለመለመችውን የአሮንን በትርና ኪዳኑ የተጻፈበትን ጽላት ይዟል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያም ውስጥ የወርቅ ማዕጠንት ነበር፤ ሁለንተናዋም በወርቅ የተለበጠች የኪዳን ታቦት፥ በእርስዋም ውስጥ መና ያለባት የወርቅ መሶብና የበቀለች የአሮን በትር የኪዳኑም ጽላት ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በውስጥዋም የወርቅ ማዕጠንትና ሁለንተናዋን በወርቅ የለበጡአት፥ የኪዳን ታቦት፥ መና ያለባት የወርቅ መሶብና የለመለመችው የአሮን በትር፥ የኪዳኑም ጽላት ነበሩባት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ውስጥ የወርቅ ማዕጠንት ነበረ ሁለንተናዋም በወርቅ የተለበጠች የኪዳን ታቦት፤ በእርስዋም ውስጥ መና ያለባት የወርቅ መሶብና የበቀለች የአሮን በትር የኪዳኑም ጽላት ነበሩ፥ |
ጽዋዎች፥ የዐመድ ማጠራቀሚያዎች፥ ጐድጓዳ ሳሕኖች፥ የዕጣን ማቅረቢያ ዕቃዎች፥ ማንደጃዎች፥ ለቅድስተ ቅዱሳን በሮችና ለቤተ መቅደሱ ውጫዊ በሮች የሚያገለግሉ ማጠፊያዎች ነበሩ። እነዚህ ሁሉ ዕቃዎች ከወርቅ የተሠሩ ናቸው።
እግዚአብሔር ከግብጽ ምድር ባወጣቸው ጊዜ ከቀድሞ አባቶቻችን ጋር ቃል ኪዳን የገባበት የድንጋይ ጽላት ለሚገኝበትም ታቦት ማኖሪያ የሚሆን ቦታ በቤተ መቅደሱ ውስጥ አዘጋጅቼአለሁ።”
የእስራኤል ሕዝብ ከግብጽ ምድር እንደ ወጡ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን በገባ ጊዜ ሙሴ በሲና ተራራ በቃል ኪዳኑ ታቦት ውስጥ ካኖራቸው ከሁለቱ የድንጋይ ጽላቶች በቀር በቃል ኪዳኑ ታቦት ውስጥ ሌላ ምንም ነገር አልነበረም።
እስራኤላውያን ከግብጽ እንደ ወጡ እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን በገባ ጊዜ ሙሴ በሲና ተራራ በቃል ኪዳኑ ታቦት ውስጥ ካስቀመጣቸው ከሁለቱ ጽላቶች በቀር በታቦቱ ውስጥ ሌላ ነገር አልነበረም።
መጋረጃውንም በድንኳኑ ጣራ ላይ በተርታ በተደረደሩት መያዣዎች ሥር ታንጠለጥለዋለህ፤ ሁለቱን የድንጋይ ጽላቶች የያዘውንም የቃል ኪዳን ታቦት ከመጋረጃው በስተኋላ በኩል ታኖረዋለህ፤ በዚህ ዐይነት መጋረጃው ቅድስት የተባለውን ስፍራ ከቅድስተ ቅዱሳኑ ይለያል፤
እግዚአብሔር ሙሴን በሲና ተራራ ላይ ማነጋገሩን ከፈጸመ በኋላ በእግዚአብሔር ጣት በድንጋይ ላይ የተጻፈባቸውን ሁለቱን የቃል ኪዳን ጽላቶች ሰጠው።
ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር ሲነጋገር ቈይቶ ስለ ነበር፥ ዐሥሩ ትእዛዞች የተጻፉባቸውን ሁለቱን የምስክር ጽላቶች ይዞ ከሲና ተራራ በወረደ ጊዜ ፊቱ አበራ፤ ለእርሱ ግን ይህ ሁሉ አይታወቀውም ነበር።
ርዝመቱ አርባ አምስት ሳንቲ ሜትር፥ የጐኑ ስፋት አርባ አምስት ሳንቲ ሜትር ቁመቱም ዘጠና ሳንቲ ሜትር የሆነ አራት ማእዘን የዕጣን መሠዊያ ከግራር እንጨት ሠራ፤ በአራቱም ማእዘን ያሉት ጒጦቹ ከእርሱ ጋር አንድ ወጥ ሆነው የተሠሩ ነበሩ።
ከመሠዊያው የሚቃጠል የእሳት ፍም በጥናው ሞልቶም ሁለት እፍኝ ጣፋጭ ሽታ ያለውን የተወቀጠ ደቃቅ ዕጣን በመውሰድ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ያግባ፤
እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፦ “የአሮንን በትር በቃል ኪዳኑ ታቦት ፊት መልሰህ አኑረው፤ ዐመፀኞች የሆኑ እስራኤላውያን በእኔ ላይ ማጒረምረማቸውን ካልተዉ እንደሚሞቱ ማስጠንቀቂያ ሆኖ ይቀመጥ።”
ከዚያም በኋላ እኔ ለክህነት የምመርጠው ሰው በትሩ በማቈጥቈጥ ትለመልማለች፤ በዚህም ዐይነት እነዚህ እስራኤላውያን በየጊዜው በአንተ ላይ ማጒረምረማቸውን እንዲያቆሙ አደርጋለሁ።”
በማግስቱ ሙሴ ወደ ድንኳኑ በገባ ጊዜ በሌዊ ነገድ ስም የቀረበችው የአሮን በትር ለምልማ አገኛት፤ ይኸውም እንቡጥ አውጥታ በማበብ የበሰለ የለውዝ ፍሬ አፍርታ ነበር።
እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር የገባው ቃል ኪዳን የተጻፈባቸውን የድንጋይ ጽላቶች ለመቀበል እኔ ወደ ተራራው ወጥቼ ነበር፤ በዚያም ምንም ነገር ሳልበላና ሳልጠጣ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ቈየሁ።
በሰማይ ያለው የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ተከፈተ፤ የእርሱም የኪዳን ታቦት በቤተ መቅደሱ ውስጥ ታየ። መብረቅ፥ ድምፅ፥ ነጐድጓድ፥ የምድር መናወጥና ታላቅም በረዶ ሆነ።
የወርቅ ጥና የያዘ ሌላ መልአክ መጣና በመሠዊያው አጠገብ ቆመ፤ በዙፋኑ ፊት ባለው የወርቅ መሠዊያ ላይ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር የሚያቀርበው ብዙ ዕጣን ተሰጠው።