ዕብራውያን 5:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወተት የሚጋት ሁሉ ሕፃን ስለ ሆነ መልካም ነገርን ከክፉ የመለየት ትምህርት አልተለማመደም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወተት የሚጋት ሁሉ ሕፃን ስለ ሆነ፣ ከጽድቅ ትምህርት ጋራ ገና አልተዋወቀም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወተት የሚጋት ሁሉ ሕፃን ስለ ሆነ የጽድቅን ቃል አያውቅም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወተትን የሚጋት ሁሉ ሕፃን ስለሆነ፥ የጽድቅን ቃል ሊያውቅ አይሻም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወተት የሚጋት ሁሉ ሕፃን ስለ ሆነ የጽድቅን ቃል አያውቅምና፤ |
በዚያን ጊዜ ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “የሰማይና የምድር ጌታ አባት ሆይ! ይህን ነገር ከጥበበኞችና ከዐዋቂዎች ሰውረህ ለአላዋቂዎች ስለ ገለጥክላቸው አመሰግንሃለሁ፤
ሕፃን በነበርኩ ጊዜ እንደ ሕፃን እናገር ነበር፤ እንደ ሕፃን አስብ ነበር፤ እንደ ሕፃን እመራመር ነበር፤ ሙሉ ሰው በሆንኩ ጊዜ ግን የሕፃንነቴን ጠባይ ተውኩ።
ወንድሞቼ ሆይ! እኔ ሳስተምራችሁ ሥጋውያንና በክርስቶስ ገና ያልጠነከራችሁ ሕፃናት እንደ መሆናችሁ መጠን ነው እንጂ መንፈሳውያን እንደ መሆናችሁ መጠን አይደለም።
ከእንግዲህ ወዲህ በሰዎች የተንኰል ሽንገላና አታላይነት በተዘጋጀ በአሳሳች የትምህርት ነፋስና ሞገድ ወዲያና ወዲህ ተገፍትረው እንደሚወሰዱ ሕፃናት አንሆንም።
ቅዱስ መጽሐፍ በሙሉ በእግዚአብሔር መንፈስ መሪነት የተጻፈ ነው፤ እርሱ እውነትን ለማስተማር፥ የተሳሳቱትን ለመገሠጽ፥ ስሕተትን ለማረምና ለትክክለኛ ኑሮ የሚበጀውን መመሪያ ለመስጠት ይጠቅማል።