ዕንባቆም 3:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምድር ላይ ቆምክ፤ በቊጣህም ሕዝቦችን ረጋገጥካቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምድር ላይ በመዓት ተመላለስህ፤ ሕዝቦችንም በቍጣ ረገጥሃቸው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቁጣ ምድርን ረገጥሃት፥ አሕዛብን በንዴት አሄድሃቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምድር ላይ በመዓት ተራመድህ፣ አሕዛብን በቍጣ አሄድሃቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምድር ላይ በመዓት ተራመድህ፥ አሕዛብን በቍጣ አሄድሃቸው። |
እነሆ፥ እኔ እንደ ስለታም፥ አዲስና፥ ጥርስ እንዳለው የመውቂያ መሣሪያ አደርግሃለሁ፤ ተራራዎችንም በማበራየት ታደቃቸዋለህ፤ ኰረብቶችንም ዳምጠህ እንደ ገለባ ታደርጋቸዋለህ።
ባቢሎን እንደ እህል መውቂያ አውድማ ትሆናለች፤ ሕዝብዋንም እንደሚወቃ እህል ጠላት ያበራያቸዋል። እኔ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ ይህን ተናግሬአለሁ።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የደማስቆ ሕዝብ ደጋግመው ስለ ሠሩት ኃጢአት ያለ ጥርጥር እቀጣቸዋለሁ፤ እነርሱ የገለዓድን ሕዝብ የብረት ጥርስ ባለው መንኰራኲር አበራይተው አሠቃይተዋቸዋል።
ሰላም አግኝተው በጸጥታ በሚኖሩ በአሕዛብ መንግሥታት ላይ እጅግ ተቈጥቼአለሁ፤ ምክንያቱም እኔ ሕዝቤን ከመቅጣት መለስ ባልኩበት ጊዜ እነዚያ የአሕዛብ መንግሥታት ሕዝቤን ከተጠበቀው በላይ አሠቃይተዋል።