Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 110:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እግዚአብሔር በቀኝህ ነው፤ በሚቈጣበት ጊዜ ነገሥታትን ድል ነሥቶ ይሰባብራቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ጌታ በቀኝህ ነው፤ በቍጣውም ቀን ነገሥታትን ያደቅቃቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ጌታ በቀኝህ፥ ነገሥታትን በቁጣው ቀን ይቀጠቅጣቸዋል።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ለሚ​ፈ​ሩት ምግ​ብን ሰጣ​ቸው፤ ኪዳ​ኑ​ንም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ያስ​ባል።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 110:5
23 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔር ሆይ! ይህን ሁሉ ክፉ ነገር በእኔ ላይ የሚናገሩትን ጠላቶቼን በዚህ ዐይነት ቅጣቸው።


እግዚአብሔር ለጌታዬ (ለመሲሑ) “ጠላቶችህን በእግርህ ማረፊያ ሥር እስከማደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ” አለው።


ዘወትር እግዚአብሔርን አስቀድማለሁ፤ እርሱም በቀኜ ስለ ሆነ አልታወከም።


ሁሉን የሚችል አምላክ ነገሥታትን በበታተነ ጊዜ በረዶ በጻልሞን ተራራዎች ላይ እንዲዘንብ አደረገ።


በሸንበቆዎች ውስጥ የሚኖሩትን እንስሶች ገሥጽ፤ ኰርማዎችና ጥጆች የመሳሰሉትን መንግሥታት ገሥጻቸው፤ ሁሉም ተንበርክከው ብራቸውን እንዲያቀርቡልህ አድርግ፤ ጦርነት ማድረግ የሚፈልጉትንም መንግሥታት በትናቸው።


በምድር ላይ ቆምክ፤ በቊጣህም ሕዝቦችን ረጋገጥካቸው።


ጌታ ኢየሱስ ይህን ሁሉ ከነገራቸው በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ። በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ።


እንግዲህ አንተ ንስሓ ባለመግባትህና እልኸኛ በመሆንህ የእግዚአብሔር ቊጣና ትክክለኛ ፍርድ በሚገለጥበት ቀን ቅጣትህ እንዲበዛ ታደርጋለህ።


አሕዛብ ተቈጡ፤ የአንተም ቊጣ መጣ፤ ሙታን ፍርድ የሚያገኙበት ጊዜም ደረሰ፤ ለአገልጋዮችህ ለነቢያትና ለቅዱሳን ስምህንም ለሚያከብሩት፥ ለታናናሾችና ለታላላቆች፥ ዋጋቸውን የምትሰጥበት ጊዜ ደረሰ፤ ምድርን ያጠፉአትን የምታጠፋበት ጊዜም ደረሰ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos