ዘፍጥረት 50:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘አባቴ ለመሞት ሲቃረብ በከነዓን ምድር ባዘጋጀው መቃብር እንድቀብረው በመሐላ ቃል አስገብቶኛል፤ ስለዚህ እዚያ ሄጄ አባቴን ቀብሬ እንድመለስ ይፈቀድልኝ ሲል ጠይቆአል’ ብላችሁ ንገሩልኝ” አላቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ‘የምሞትበት ጊዜ ስለ ተቃረበ፣ በከነዓን ምድር ራሴ ቈፍሬ በአዘጋጀሁት መቃብር እንድትቀብረኝ’ ሲል አባቴ አስምሎኛል፤ ስለዚህ ወደዚያ ሄጄ አባቴን ልቅበር፤ ከዚያም እመለሳለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አባቴ፦ ‘እነሆ እኔ እሞታለሁ፥ በቈፈርሁት መቃብር በከነዓን ምድር ከዚያ ቅበረኝ’ ሲል አስምሎኛል። አሁንም ወጥቼ አባቴን ልቅበርና ልመለስ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አባቴ ሳይሞት አምሎኛል፤ እንዲህ ሲል፦ ‘እነሆ እኔ እሞታለሁ፤ በቈፈርሁት መቃብር በከነዓን ምድር በዚያ ቅበረኝ።’ አሁንም ወጥቼ አባቴን ልቅበርና ልመለስ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አባቴ አምሎኛልን እንዲ ሲል፦ እነሆ እኔ እሞታለሁ በቋፈርሁት መቃብር በከነዓን ምድር ከዚያ ቅበረኝ። አሁንም ወጥቼ አባቴን ልቅበርና ልመለስ። |
ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ዮሴፍን እንዲህ አለው፤ “እነሆ፥ እኔ የምሞትበት ጊዜ ተቃርቦአል፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ነው፤ ወደ ቀድሞ አባቶቻችሁም ምድር ይመልሳችኋል፤
ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ወንድሞቹን እንዲህ አላቸው፤ “እነሆ እኔ የምሞትበት ጊዜ ተቃርቦአል፤ እናንተን ግን እግዚአብሔር በረድኤት ይጐበኛችኋል፤ ከዚህም አገር አውጥቶ ለአብርሃም፥ ለይስሐቅና ለያዕቆብ ለመስጠት በመሐላ ቃል ወደ ገባላቸው ምድር ይመልሳችኋል።
ሬሳውም በልዩ ቅመማ ቅመምና በሽቶ ታሽቶ እርሱ ራሱ በዳዊት ከተማ ከአለት አስፈልፍሎ ባሠራው መቃብር ተቀበረ፤ ስለ ክብሩም ብዙ እንጨት ከምረው በማንደድ ታላቅ ለቅሶ አደረጉለት።
ወደ ከፍተኛ ስፍራዎች መውጣት ያስፈራሃል፤ በእግር መጓዝም አደገኛ ይሆንብሃል፤ ጠጒርህ እንደ ለውዝ አበባ ነጭ ይሆናል፤ ራስህን ችለህ መራመድ አቅቶህ እንደ አሮጌ ኩብኩባ ትጐተታለህ፤ ፍላጎትህ መቀስቀሱ ይቀራል። ድምፅ እንኳ ከእንቅልፍህ ይቀሰቅስሃል። ሰውም ወደ ዘለዓለማዊ መኖሪያው ይሄዳል፤ አልቃሾችም በየመንገዱ እያለቀሱ ይሸኙታል።
እንግዲህ፥ አንድ ሰው መቶ ልጆች ቢወልድ፥ ረጅም ዕድሜ አግኝቶ ብዙ ዘመን በሕይወት ቢኖርም፥ እንዲደሰትበት ከሚያስፈልገው ነገር ሁሉ ድርሻውን ሳያገኝ ቀርቶ በመጨረሻም በክብር ለመቀበር ሳይበቃ ቢቀር፥ እኔ ስለ እርሱ አዝናለሁ፤ ከእንደዚህ ያለውም ሰው ይልቅ በእናቱ ማሕፀን ሞቶ የተወለደ ጭንጋፍ ይሻላል አልኩ።
ከዚህም በኋላ ሳኦል ዮናታንን “ያደረግኸው ነገር ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀ። ዮናታንም “በበትሬ ጫፍ አስነክቼ ጥቂት ማር. ቀምሻለሁ እነሆ በዚህ እገኛለሁ፤ ለመሞትም ዝግጁ ነኝ” አለ።