ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ “አጣድ” ተብላ ወደምትጠራው አውድማ ደረሱ፤ እዚያም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በመጮኽ አለቀሱ፤ ዮሴፍም እዚያ ሰባት ቀን ሙሉ የሐዘን ውሎ አደረገ።
ዘፍጥረት 50:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መድኃኒት ቀማሚዎቹም በሀገሩ ልማድ መሠረት ሬሳውን ለማድረቅ አርባ ቀን ፈጀባቸው። ግብጻውያን ሰባ ቀን ሙሉ አለቀሱለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሬሳው እንዳይፈርስ መድኀኒት መቀባቱ በአገሩ ልማድ መሠረት አርባ ቀን ወሰደባቸው፤ ግብጻውያንም ሰባ ቀን አለቀሱለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መድኃኒት ቀማሚዎቹም በሀገሩ ልማድ መሠረት ሬሳውን ለማድረቅ አርባ ቀን ፈጀባቸው። ግብጻውያን ሰባ ቀን ሙሉ አለቀሱለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አርባ ቀንም ፈጸሙለት፤ ሽቱ የሚቀቡበትን ቀን እንዲሁ ይቈጥራሉና፤ የግብፅም ሰዎች ሰባ ቀን አለቀሱለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አርባ ቀንም ፈጸሙለት የሽቱ መደረጊያው ወራት እንደዚሁ ይፈጸማልን የግብፅም ሰዎች ሰባ ቅን አለቀሱለት። |
ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ “አጣድ” ተብላ ወደምትጠራው አውድማ ደረሱ፤ እዚያም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በመጮኽ አለቀሱ፤ ዮሴፍም እዚያ ሰባት ቀን ሙሉ የሐዘን ውሎ አደረገ።
ልብስዋን ትለውጥ፤ እርስዋም ከአንተ ጋር በቤትህ ተቀምጣ እስከ አንድ ወር ድረስ በጦርነት ስለሞቱት ወላጆችዋ ታልቅስ፤ ከዚያም በኋላ ሚስት አድርገህ ታገባታለህ።