Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘዳግም 34:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 የእስራኤልም ሕዝብ የሐዘኑ ጊዜ እስከሚያበቃ ድረስ ለሙሴ በማዘን ሠላሳ ቀን በሞአብ ሜዳ አለቀሱለት።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 የልቅሶውና የሐዘኑ ጊዜ እስኪያበቃ ድረስ፣ እስራኤላውያን ለሙሴ በሞዓብ ሜዳ ሠላሳ ቀን አለቀሱለት።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 የእስራኤልም ሕዝብ የሐዘኑ ጊዜ እስከሚያበቃ ድረስ ለሙሴ በማዘንሠላሳ ቀን በሞዓብ ሜዳ አለቀሱለት።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች በዮ​ር​ዳ​ኖስ በኢ​ያ​ሪኮ አቅ​ራ​ቢያ በሞ​ዓብ ሜዳ ሠላሳ ቀን ለሙሴ አለ​ቀ​ሱ​ለት፤ ለሙ​ሴም ያለ​ቀ​ሱ​ለት የል​ቅ​ሶው ወራት ተፈ​ጸመ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 የእስራኤልም ልጆች በሞዓብ ሜዳ ሠላሳ ቀን ለሙሴ አለቀሱለት፤ ለሙሴም ያለቀሱለት የልቅሶው ወራት ተፈጸመ።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 34:8
9 Referencias Cruzadas  

ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ “አጣድ” ተብላ ወደምትጠራው አውድማ ደረሱ፤ እዚያም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በመጮኽ አለቀሱ፤ ዮሴፍም እዚያ ሰባት ቀን ሙሉ የሐዘን ውሎ አደረገ።


መድኃኒት ቀማሚዎቹም በሀገሩ ልማድ መሠረት ሬሳውን ለማድረቅ አርባ ቀን ፈጀባቸው። ግብጻውያን ሰባ ቀን ሙሉ አለቀሱለት።


የኦርዮ ሚስት ባልዋ እንደ ተገደለ በሰማች ጊዜ በማልቀስ አዘነችለት፤


ጻድቃን ሲሞቱ ማንም ትኲረት አይሰጠውም፤ ደጋግ ሰዎች በሞት ሲወሰዱ ከክፉ ነገር እንዲድኑ የተወሰዱ መሆናቸውን ማንም ሰው ሊያስተውለው አይችልም።


መላው ማኅበር አሮን እንደ ሞተ ሰሙ፤ እስከ ሠላሳ ቀንም ድረስ በሐዘን አለቀሱለት።


አንዳንድ መንፈሳውያን ሰዎች እስጢፋኖስን ቀበሩት፤ በታላቅ ድምፅም እየጮኹ አለቀሱለት።


ሙሴም በሞተ ጊዜ ዕድሜው መቶ ኻያ ዓመት ነበር፤ ነገር ግን ዐይኑ ያልፈዘዘና ጒልበቱም ያልደከመ ገና ብርቱ ሰው ነበር።


ሙሴ የእርሱ ተተኪ እንዲሆን እጆቹን በመጫን ሹሞት ስለ ነበር የነዌ ልጅ ኢያሱ በጥበብ የተሞላ ሆነ፤ የእስራኤልም ሕዝብ ለኢያሱ ታዘዘለት፤ እግዚአብሔር በሙሴ አማካይነት የሰጣቸውንም ትእዛዝ ጠበቁ።


ሳሙኤል ሞተ፤ መላው እስራኤላውያንም በአንድነት መጥተው አለቀሱለት፤ ከዚያም በኋላ በራማ በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ቀበሩት። ከዚያም በኋላ ዳዊት ወደ ፋራን ምድረ በዳ ሄደ፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos