ዘፍጥረት 49:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ዮሴፍ፥ በውሃ ምንጭ አጠገብ ተተክሎ፥ ሐረጎቹ በግድግዳ ላይ እንደሚዘረጉ ፍሬያማ ዛፍ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ዮሴፍ፤ ፍሬያማ የወይን ተክል፣ በምንጭ ዳር የተተከለ ወይን ነው። ሐረጎቹ ቅጥርን ያለብሳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮሴፍ ትንሹ የፍሬ ዛፍ ነው፥ በምንጭ አጠገብ የሚያፈራ የፍሬ ዛፍ፥ አረጎቹ በቅጥር ላይ ያድጋሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ዮሴፍ የሚያድግ ልጅ ነው፤ ለእኔ በጣም የተወደደ የሚቀናልኝና የሚያድግልኝ ልጅ ነው፤ ወደ እኔ የሚመለስም ጐልማሳ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮሴፍ ትንሹ የፍሬ ዛፍ ነው፥ በምንጭ አጠገብ የሚያፈራ የፍሬ ዛፍ አረጎቹ በቅጥር ላይ ያድጋሉ። |
ለዮሴፍ በግብጽ ከተወለዱት ከሁለቱ ወንዶች ልጆች ጋር፥ ከያዕቆብ ጋር ወደ ግብጽ የገቡት የያዕቆብ ልጆችና የልጅ ልጆች ቊጥር በአጠቃላይ ሰባ ነበር።
ጥቂት ጊዜ ካለፈ በኋላ “አባትህ ታሞአል” ተብሎ ለዮሴፍ ተነገረው፤ ስለዚህ ዮሴፍ ሁለቱን ልጆቹን ምናሴንና ኤፍሬምን ይዞ ያዕቆብን ለማየት ሄደ።
ከዚህ በኋላ ዮሴፍን እንዲህ ሲል ባረከው፦ “አባቶቼ አብርሃምና ይስሐቅ መንገዱን በመከተል ያገለገሉትና እኔንም ሕይወቴን ሙሉ እስከ ዛሬ ድረስ እረኛ ሆኖ የጠበቀኝ አምላክ እነዚህን ልጆች ይባርክ!
እኔን ከጒዳት ሁሉ ያዳነኝ መልአክ እነርሱንም ይጠብቃቸው። የእኔ ስም፥ የአባቶቼም የአብርሃምና የይስሐቅ ስም በነዚህ ልጆች ሲታወስ ይኑር፤ ዘራቸውም በምድር ላይ ይብዛ።”
ያዕቆብ ንግግሩን በመቀጠል እንዲህ አለ፤ “ልጄ ዮሴፍ እኔ እዚህ ከመምጣቴ በፊት በግብጽ ምድር የተወለዱልህ ሁለት ልጆችህ ከእንግዲህ የእኔ ልጆች ናቸው፤ ኤፍሬምና ምናሴ እንደ ሮቤልና እንደ ስምዖን ይቈጠራሉ።
ቅርንጫፎቹ ብርቱዎች ስለ ነበሩ፥ በትረ መንግሥት እስከሚገኝባቸው ድረስ አደጉ፤ የወይን ተክሉም ጥቅጥቅ ካለው ደን በላይ አደገ፤ ርዝመቱ ከብዙ ቅርንጫፎች ጋር ከፍ ብሎ ታየ።
በወንድሞቹ መካከል ፍሬያማ ቢሆንም የእግዚአብሔር ቅጣት የሆነው የምሥራቁ ነፋስ ከምድረ በዳ ተነሥቶ ይመጣል፤ ምንጩ ይቆማል፤ ወንዙም ይደርቃል። ነፋሱም የነበሩትን ውድ ዕቃዎች ሁሉ ገፎ ይወስድበታል።