ዘፍጥረት 49:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ የያዕቆብ ልጆች፥ በአንድነት ተሰብስባችሁ ስሙ፤ አባታችሁ እስራኤል የሚነግራችሁንም አድምጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እናንተ የያዕቆብ ልጆች ሆይ፤ ተሰብሰቡና ስሙ፤ አባታችሁ እስራኤልንም ስሙ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እናንት የያዕቆብ ልጆች ተሰብሰቡ፥ ስሙም፥ አባታችሁ እስራኤልንም አድምጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናንት የያዕቆብ ልጆች ኑ፥ ተሰብሰቡ፤ ስሙም፤ አባታችሁ እስራኤልንም አድምጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እናንት የያዕቆብ ልጆች ተሰብስቡ፥ ስሙም አባታችሁ እስራኤልንም አድምጡ። |
“ሁላችሁም ተሰብስባችሁ ኑና አድምጡ! ስለ እነዚህ ነገሮች አስቀድሞ የተናገረ ከጣዖቶች መካከል የትኛው ነው? የእግዚአብሔር ተመራጭ በባቢሎን ላይ ዓላማውን ይፈጽማል። ኀይሉም በባቢሎናውያን ላይ ይሆናል።