ከእነርሱም በኋላ የወጡት ሰባት የከሱትና አስከፊዎቹ ላሞች ሰባት ዓመቶች ናቸው፤ እንዲሁም ሰባቱ የቀጨጩና በበረሓ ነፋስ ተመተው የሰለቱ የእሸት ዛላዎች ሰባት ዓመቶች ናቸው፤ የሁለቱም ትርጒም አንድ ነው፤ ይኸውም ሰባት የራብ ዓመቶች ናቸው።
ዘፍጥረት 47:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮሴፍ ለሕዝቡ እንዲህ አላቸው፤ “እነሆ፥ እንግዲህ እናንተንና መሬታችሁን ለፈርዖን ስለ ገዛሁ ዘር ውሰዱና በመሬታችሁ ላይ ዝሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዮሴፍ ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፤ “እነሆ፣ ዛሬ እናንተንም መሬታችሁንም ለፈርዖን ገዝቻችኋለሁና ይህን ዘር ወስዳችሁ በመሬት ላይ ዝሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮሴፍም ሕዝቡን እንዲህ አለ፦ “እነሆ ዛሬ እናንተንና ምድራችሁን ለፈርዖን ገዝቻችኋለሁ፥ ዘር ውሰዱና ምድሪቱን ዝሩ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዮሴፍም የግብፅን ሰዎች ሁሉ እንዲህ አላቸው፥ “እነሆ ዛሬ እናንተንና ምድራችሁን ለፈርዖን ገዝቻችኋለሁ፤ ለእናንተ ዘር ውሰዱና ምድሪቱን ዝሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዮሴፍም ሕዝቡን እንዲህ አለ፦ እነሆ ዛሬ እናንተንና ምድራችሁን ለፈርዖን ገዝቻችኍለሁ ዘር ውሰዱና |
ከእነርሱም በኋላ የወጡት ሰባት የከሱትና አስከፊዎቹ ላሞች ሰባት ዓመቶች ናቸው፤ እንዲሁም ሰባቱ የቀጨጩና በበረሓ ነፋስ ተመተው የሰለቱ የእሸት ዛላዎች ሰባት ዓመቶች ናቸው፤ የሁለቱም ትርጒም አንድ ነው፤ ይኸውም ሰባት የራብ ዓመቶች ናቸው።
ነገር ግን በመከር ጊዜ ከምታመርቱት ከአምስት አንዱን እጅ ለፈርዖን መስጠት አለባችሁ፤ የቀረው አራት አምስተኛው እጅ ግን ለመሬታችሁ ዘር፥ ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ ለቤተሰባችሁም ሁሉ ምግብ ይሁናችሁ።”
አቈይቶ በውድ ዋጋ ለመሸጥ እህሉን የሚያከማች ሰው፥ በሕዝብ ዘንድ የተረገመ ይሆናል፤ እህሉን ለገበያ የሚያቀርብ ሰው ግን፥ በሕዝብ ዘንድ የተመሰገነ ይሆናል።
“ዝናብና ደቃቅ በረዶ ከሰማይ ወርደው ምድርን በማርካት ፍሬ እንድታፈራ እንደሚያደርጓትና ለዘሪው ዘርን፥ ለበላተኛውም ምግብን ሳይሰጡ ወደ ሰማይ እንደማይመለሱ፥