ዘፍጥረት 46:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጌሴም ምድር እንዲቀበለው ያዕቆብ ይሁዳን ወደ ዮሴፍ አስቀድሞ ላከው፤ እነርሱ ጌሴም በደረሱ ጊዜ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብም ወደ ጌሤም ለመሄድ መመሪያን ይቀበል ዘንድ ይሁዳን አስቀድሞ ወደ ዮሴፍ ላከው። እነርሱም ጌሤም ሲደርሱ፣ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በጌሴም ምድር እንዲቀበለው ያዕቆብ ይሁዳን ወደ ዮሴፍ አስቀድሞ ላከው፤ ወደ ጌሤም ምድርም ደረሱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይሁዳንም ኤሮስ በምትባል በራምሴ ከተማ እንዲቀበለው በፊቱ ወደ ዮሴፍ ላከው፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይሁዳንም በጌሤም እንዲቀበለው በፊቱ ወደ ዮሴፍም ላከ ወደ ጌሤም ምድርም ደረሱ። |
ይሁዳም አባቱን እንዲህ አለ፤ “ልጁን በእኔ ኀላፊነት አብሮን እንዲሄድ አድርግ፥ ሳንዘገይ አሁኑኑ ጒዞ እንጀምር፤ ይህ ከሆነ፥ እኛም አንተም ልጆቻችንም ሁሉ በራብ ከመሞት እንድናለን።
ልጆችህን፥ የልጅ ልጆችህን፥ በጎችህን፥ ፍየሎችህን፥ ከብቶችህን ሌላም ያለህን ነገር ሁሉ ይዘህ ና፥ በእኔው አቅራቢያ በሚገኘው በጌሴም ምድር ትኖራለህ።
‘እኛ ልክ እንደ ቀድሞ አባቶቻችን ከልጅነታችን ጀምሮ የምንተዳደረው በግ በማርባት ነው’ ብላችሁ መልሱለት። በግ አርቢዎች በግብጻውያን ዘንድ የተናቁ ስለ ሆኑ ይህን በመናገር በጌሴም ምድር ለመኖር ፈቃድ ታገኛላችሁ።”
ዮሴፍም ወደ ፈርዖን ሄዶ “አባቴና ወንድሞቼ በጎቻቸውንና ፍየሎቻቸውን ከብቶቻቸውንና ሌላም ያላቸውን ነገር ሁሉ ይዘው ከከነዓን ወደዚህ መጥተዋል፤ አሁንም በጌሴም ምድር ይገኛሉ” አለው።