ወንዶችና ሴቶች ልጆቹ ሁሉ ሊያጽናኑት ወደ እርሱ መጡ፤ እርሱ ግን “ለልጄ እያለቀስሁ ወደ ሙታን ዓለም እወርዳለሁ” በማለት መጽናናትን እምቢ አለ። ስለዚህ ስለ ልጁ ማዘኑን ቀጠለ።
ዘፍጥረት 44:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብላቴናው ከእኛ ጋር እንደሌለ ሲያይ ይሞታል፤ እኛ አገልጋዮችህም የአገልጋይህን የአባታችንን ሽበት በሐዘን ወደ መቃብር እናወርዳለን፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የልጁን ከእኛ ጋራ አለመኖር ሲያይ አባቴ ይሞታል። ከዚህም የተነሣ እኛ አገልጋዮችህ የአባታችንን ሽበት በመሪር ሐዘን ወደ መቃብር እናወርደዋለን። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የልጁን ከእኛ ጋር አለመኖር ሲያይ አባቴ ይሞታል። ከዚህም የተነሣ እኛ አገልጋዮችህ የአባታችንን ሽበት በመሪር ኀዘን ወደ መቃብር እናወርደዋለን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ብላቴናው ከእኛ ጋር እንደሌለ በአየ ጊዜ ይሞታል፤ አገልጋዮችህም የአገልጋይህን የአባታችንን እርጅና በኀዘን ወደ መቃብር እናወርዳለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ባሪያዎህም የባሪያህን የአባታችንን ሽበት በኅዘን ወደ መቃብር ያወርዳሉ። |
ወንዶችና ሴቶች ልጆቹ ሁሉ ሊያጽናኑት ወደ እርሱ መጡ፤ እርሱ ግን “ለልጄ እያለቀስሁ ወደ ሙታን ዓለም እወርዳለሁ” በማለት መጽናናትን እምቢ አለ። ስለዚህ ስለ ልጁ ማዘኑን ቀጠለ።
ያዕቆብም “ምንም ቢሆን ከእናንተ ጋር አይሄድም፤ ወንድሙ ሞቶአል፤ የቀረው እርሱ ብቻ ነው፤ በመንገድ አንድ ጒዳት ቢደርስበት በእርጅናዬ ዘመን በመሪር ሐዘን ወደ መቃብር እንድወርድ ታደርጉኛላችሁ” አላቸው።
እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሚሆን ሐዘን ወደ መዳን የሚመራ በንስሓ የሚገኘውን ለውጥ ስለሚያስገኝ ጸጸትን አያስከትልም፤ ዓለማዊ ሐዘን ግን ሞትን ያመጣል።
ዳዊትም አብያታርን “እኔ በዚያ ቀን ኤዶማዊውን ዶይቅን እዚያ ባየሁት ጊዜ ሁሉን ነገር ለሳኦል እንደሚነግረው ዐውቄ ነበር፤ ከዚህም የተነሣ ስለ ዘመዶችህ ሁሉ እልቂት እኔ ተጠያቂነት አለብኝ፤