ዘፍጥረት 43:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይሁዳ ግን ለአባቱ እንዲህ ብሎ መለሰለት፥ “ሰውየው ‘ወንድማችሁን ይዛችሁ ካልመጣችሁ እፊቴ እንዳትቀርቡ’ በማለት በብርቱ አስጠንቅቆናል፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይሁዳ ግን እንዲህ አለው፤ “ያ ሰውየው ‘ወንድማችሁን ይዛችሁ ካልመጣችሁ ዳግመኛ ፊቴን አታዩም’ ብሎ በጥብቅ አስጠንቅቆናል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይሁዳ ግን እንዲህ አለው፤ “ያ ሰው ‘ወንድማችሁን ይዛችሁ ካልመጣችሁ ዳግመኛ ፊቴን አታዩም’ ብሎ በጥብቅ አስጠንቅቆናል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይሁዳም እንዲህ አለው፥ “የሀገሩ ጌታ ያ ሰው፦ ‘ወንድማችሁ ከእናንተ ጋር ከአልመጣ ፊቴን አታዩም’ ብሎ በምስክር ፊት አዳኝቶብናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይሁዳም እንዲህ አለው፦ ያ ሰው፦ ወንድማችሁ ከእናንተ ጋር ካልሆነ ፊቴን አታዪም ብሎ በብርቱ ቃል አስጠነቀቀን። |
ጌታችንም ለአንተ ለጌታችን ነግረንህ አገልጋዮቹን ‘ታናሽ ወንድማችሁን ይዛችሁ ካልመጣችሁ ዳግመኛ በፊቴ አትቀርቡም’ ብለህ በብርቱ አስጠነቀቅከን።
ይሁን እንጂ ንጉሡ፥ አቤሴሎም በቤተ መንግሥት ውስጥ እንዳይኖር ትእዛዝ ሰጠ፤ ደግሞም ንጉሡ “ከቶ እርሱን ማየት አልፈልግም” አለ። ስለዚህ አቤሴሎም በራሱ ቤት ኖረ፤ ወደ ንጉሡም ፊት ቀርቦ አልታየም።
አቤሴሎምም “አንተ እኔ ስጠራህ ስላልመጣህ ነው፤ ወደ ንጉሡ ሄደህ ‘ከገሹር ወጥቼ ወደዚህ ለምን መጣሁ? እዚያው ቈይቼ ብሆን ኖሮ በተሻለኝ ነበር’ ብለህ ስለ እኔ ሁኔታ ጠይቅልኝ፤ እንዲሁም ከንጉሡ ጋር መገናኘት እችል ዘንድ ሁኔታዎችን አመቻችልኝ፤ እኔ በደለኛ ሆኜ ከተገኘሁ ሞት ይፍረድብኝ” አለው።
ዳዊትም “መልካም ነው! ከአንተ ጋር ስምምነት አደርጋለሁ፤ ነገር ግን አንተ በቅድሚያ የምትፈጽምልኝ ነገር አለ፤ ይኸውም ወደ እኔ በምትመጣበት ጊዜ የሳኦልን ልጅ ሜልኮልን ይዘህ ካልመጣህ መገናኘት አንችልም” አለው።
“እስከ አሁን በእናንተ ሁሉ መካከል እየተዘዋወርኩ የእግዚአብሔርን መንግሥት እሰብክ ነበር፤ ከእንግዲህ ወዲህ ግን ከእናንተ ማንም ከቶ ፊቴን እንደማያይ ዐውቃለሁ።
በግብጽ ያለውን የሕዝቤን ጽኑ መከራ በእርግጥ አይቼአለሁ፤ የጭንቀት ጩኸታቸውንም ሰምቻለሁ፤ ስለዚህ ላድናቸው ወርጃለሁ፤ አሁንም ና! እኔ አንተን ወደ ግብጽ እልክሃለሁ።’