Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 43:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ይሁዳ ግን እንዲህ አለው፤ “ያ ሰውየው ‘ወንድማችሁን ይዛችሁ ካልመጣችሁ ዳግመኛ ፊቴን አታዩም’ ብሎ በጥብቅ አስጠንቅቆናል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ይሁዳ ግን እንዲህ አለው፤ “ያ ሰው ‘ወንድማችሁን ይዛችሁ ካልመጣችሁ ዳግመኛ ፊቴን አታዩም’ ብሎ በጥብቅ አስጠንቅቆናል፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ይሁዳ ግን ለአባቱ እንዲህ ብሎ መለሰለት፥ “ሰውየው ‘ወንድማችሁን ይዛችሁ ካልመጣችሁ እፊቴ እንዳትቀርቡ’ በማለት በብርቱ አስጠንቅቆናል፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ይሁ​ዳም እን​ዲህ አለው፥ “የሀ​ገሩ ጌታ ያ ሰው፦ ‘ወን​ድ​ማ​ችሁ ከእ​ና​ንተ ጋር ከአ​ል​መጣ ፊቴን አታ​ዩም’ ብሎ በም​ስ​ክር ፊት አዳ​ኝ​ቶ​ብ​ናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ይሁዳም እንዲህ አለው፦ ያ ሰው፦ ወንድማችሁ ከእናንተ ጋር ካልሆነ ፊቴን አታዪም ብሎ በብርቱ ቃል አስጠነቀቀን።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 43:3
13 Referencias Cruzadas  

አንተ ግን እኛን አገልጋዮችህን፣ ‘ታናሽ ወንድማችሁ ዐብሯችሁ ወደዚህ ካልመጣ ዳግመኛ ፊቴን አታዩም’ አልኸን።


እርሱን የማትልከው ከሆነ ግን እኛም ወደዚያ አንወርድም፤ ያም ሰው፣ ‘ወንድማችሁን ይዛችሁ ካልመጣችሁ ዳግመኛ ፊቴን አታዩም’ ብሎናል።”


ከሁሉም በላይ ልባቸውን የነካው፣ ከእንግዲህ ወዲህ ፊቱን እንደማያዩ የተናገራቸው ቃል ነበር። ከዚያም እስከ መርከቡ ድረስ ሸኙት።


“አሁንም ቢሆን፣ በመካከላችሁ ተዘዋውሬ የእግዚአብሔርን መንግሥት የሰበክሁላችሁ፣ እናንተ ሁላችሁ ከእንግዲህ ወዲያ ፊቴን እንደማታዩ ዐውቃለሁ።


በግብጽ ያለውን የሕዝቤን መከራ በርግጥ አይቻለሁ፤ የጭንቅ ጩኸታቸውን ሰምቻለሁ፤ ላድናቸውም ወርጃለሁ። አሁንም ና፤ ወደ ግብጽ መልሼ እልክሃለሁ።’


አቤሴሎምም፣ ኢዮአብን፣ “ከጌሹር ለምን መጣሁ? ‘ለእኔ እስካሁንም እዚያው ብሆን ይሻለኝ ነበር ብሏል ብለህ እንድትነግርልኝ ወደ ንጉሡ እልክህ ዘንድ ወደ እኔ ና’ ብዬ አስጠራሁህ፤ አሁንም ቢሆን፤ የንጉሡን ዐይን ማየት እፈልጋለሁ፤ ምንም ዐይነት በደል ከተገኘብኝ ይግደለኝ” አለው።


አቤሴሎም የንጉሡን ዐይን ሳያይ ሁለት ዓመት በኢየሩሳሌም ኖረ።


ንጉሡ ግን፣ “እዚያው እቤቱ ይሂድ፤ ዐይኔን ማየት የለበትም” አለ። ስለዚህም አቤሴሎም ወደ ቤቱ ሄደ፤ የንጉሡንም ፊት አላየም።


ዳዊትም፣ “ይሁን ዕሺ፣ ከአንተ ጋራ ስምምነቱን አደርጋለሁ፤ ነገር ግን ከአንተ አንዲት ነገር እሻለሁ፤ ይኸውም ወደ እኔ ስትመጣ በመጀመሪያ የሳኦልን ሴት ልጅ ሜልኮልን ይዘህልኝ እንድትመጣ ነው፤ አለዚያ ግን ወደ እኔ እንዳትመጣ” አለ።


ከግብጽ ያመጡትንም እህል በልተው ከጨረሱ በኋላ፣ አባታቸው “እስኪ እንደ ገና ወርዳችሁ፣ ጥቂት እህል ሸምቱልን” አላቸው።


ወንድማችን ከእኛ ጋራ እንዲወርድ ከፈቀድህ ወደዚያ ሄደን እህል እንሸምትልሃለን፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios