ዘፍጥረት 41:45 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፈርዖን ለዮሴፍ “ጻፍናት ፐዕናሕ” የሚል መጠሪያ ስም አወጣለት፤ አስናት ተብላ የምትጠራውን የጶጢፌራን ልጅ በሚስትነት ሰጠው፤ ጶጢፌራ ኦን ተብሎ በሚጠራው ከተማ ካህን ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፈርዖንም ዮሴፍን ጸፍናት ፐዕናህ ብሎ ስም አወጣለት። እንዲሁም የሄልዮቱ ኦን ከተማ ካህን የጶጥፌራ ልጅ አስናትን አጋባው። ዮሴፍም በመላዪቱ የግብጽ ምድር ተዘዋወረ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፈርዖንም ዮሴፍን “ጸፍናት ፐዕናህ” ብሎ ስም አወጣለት። እንዲሁም የሄልዮቱጠ ከተማ ካህን የጶጥፌራ ልጅ አስናትን አጋባው። ዮሴፍም በመላዪቱ የግብጽ ምድር ተዘዋወረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈርዖንም የዮሴፍን ስም “እስፍንቶፎኔህ” ብሎ ጠራው፤ የሄልዮቱ ከተማ ካህን የጴጤፌራ ልጅ የምትሆን አስኔትንም ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈርዖንም የዮሴፍን ስም ጸፍናት ፐዕናህ ብሎ ጠራው የሄልዮቱ ከተማ ካህን የዾጥፌራ ልጅ የምትሆን አስናትን አጋባው። ዮሴፍም በግብፅ ምድር ሁሉ ወጣ። |
ሰባቱ የራብ ዓመቶች ከመጀመራቸው በፊት፥ ዮሴፍ ከጶጢፌራ ልጅ ከአስናት ሁለት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ ጶጢፌራ ኦን ተብሎ በሚጠራው ከተማ ካህን ነበረ።
አንድ የምድያም ካህን ሰባት ሴቶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም ውሃ ለመቅዳትና በገንዳ እየሞሉ የአባታቸውን በጎችና ፍየሎች ለማጠጣት ወደዚያ መጡ።
በግብጽ ውስጥ በሄሊዮፖሊስ ከተማ የሚገኙትን ከድንጋይ የተሠሩ ሐውልቶችን ይደመስሳል፤ የግብጻውያንን ጣዖቶችንና ቤተ መቅደሶችን ያቃጥላል።”
ከእነርሱም አንዱ አጋቦስ የሚባለው ተነሥቶ በዓለም ሁሉ ታላቅ ራብ እንደሚሆን በመንፈስ ቅዱስ አነሣሽነት ትንቢት ተናገረ፤ ይህም የሆነው በሮም ንጉሠ ነገሥት በቀላውዴዎስ ዘመን ነበር።