ዘፍጥረት 4:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መልካም ነገር አድርገህ ቢሆን ኖሮ ተቀባይነት አይኖርህም ነበርን? መልካም ባታደርግ ግን ኃጢአት በበርህ ላይ ያደባል፤ በቊጥጥሩ ሥር ሊያደርግህም ይፈልጋል፤ ሆኖም አንተ ልታሸንፈው ይገባል።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም መልካም ብታደርግ ተቀባይነትን አታገኝምን? መልካም ባታደርግ ግን፣ ኀጢአት በደጅህ እያደባች ናት፤ ልታሸንፍህ ትፈልጋለች፤ አንተ ግን ተቈጣጠራት።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መልካም ነገር አድርገህ ቢሆን ኖሮ ተቀባይነት አይኖርህም ነበርን? መልካም ባታደርግ ግን ኃጢአት በደጅ ታደባለች፥ ፍላጎትዋም ወደ አንተ ነው፥ አንተ ግን በእርሷ ልትሰለጥንባት ይገባል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእውነት ያመጣህልኝ አይደለም፤ አግባብስ በእውነት ታመጣልኝ ዘንድ ነበር። በደልህ፤ እንግዲህ ዝም በል፤ የወንድምህ መመለሻው ወደ አንተ ነው፤ አንተም ትሰለጥንበታለህ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) መልካም ባታደርግ ግን ኂጢአት በደጅ ታደባለች፤ ፈቃድዋም ወደ አንተ ግን በእርስዋ ንገሥባት። |
ሴቲቱንም፥ “በእርግዝናሽ ወራት ጭንቀትሽን፥ በምትወልጂበትም ጊዜ የምጥ ሥቃይሽን አበዛሁ፤ ይህም ሁሉ ሆኖ ፍላጎትሽ ለባልሽ ይሆናል። ለእርሱም ታዛዥ ትሆኚአለሽ” አላት።
በሶርያው ንጉሥ አዛሄል ላይ በታወጀው ጦርነት፥ ንጉሥ አካዝያስ የእስራኤል ንጉሥ ኢዮራም ተባባሪ በመሆን ዘመተ፤ የሁለቱም ነገሥታት ሠራዊት ከሶርያውያን ሠራዊት ጋር በገለዓድ በምትገኘው በራሞት ጦርነት በገጠመ ጊዜ ኢዮራም በውጊያው ላይ ቈሰለ፤
ስለዚህ አሁን ሰባት ኰርማዎችንና ሰባት አውራ በጎችን ይዛችሁ ወደ አገልጋዬ ወደ ኢዮብ ሂዱ፤ እዚያም ስለ ራሳችሁ ኃጢአት የሚቃጠል መሥዋዕት አቅርቡ፤ አገልጋዬ ኢዮብ ይጸልይላችኋል፤ እኔም ጸሎቱን ሰምቼ በበደላችሁ መጠን አልቀጣችሁም፤ እናንተ እንደ ኢዮብ ስለ እኔ ትክክል የሆነውን ነገር አልተናገራችሁም።”
ዐመፀኞች የሚያቀርቡት መሥዋዕት በእግዚአብሔር ዘንድ አጸያፊ ነው፤ በተለይም በክፉ አሳብ ተነሣሥተው የሚያቀርቡለት መሥዋዕት የበለጠ አጸያፊ ነው።
ስለዚህም እግዚአብሔር ወደ ሰሜን ሄጄ ለእስራኤል እንድነግራት ያዘዘኝ ይህ ነው፤ “እምነት የማይጣልብሽ እስራኤል ሆይ! ወደ እኔ ተመለሺ፤ እኔ ምሕረቴ የበዛ ስለ ሆነ አልቈጣም፤ በአንቺ ላይ የምቈጣውም ለዘለዓለም አይደለም።
ከሳባ የሚያመጡልኝ ዕጣን፥ ከሩቅ አገሮች የሚያመጡልኝ ቅመማቅመም ሁሉ ለእኔ ምን ይረባኛል? መባቸውን አልቀበለውም፤ መሥዋዕታቸውም ደስ አያሰኘኝም።
ኃጢአትን ይቅር የሚል፥ በቀሪውም ሕዝቡ ላይ በደልን የማይቈጥር እንደ አንተ ያለ አምላክ ማን ነው? ምሕረት ማድረግ ስለሚያስደስትህ ቊጣህ ለዘለዓለም የሚቈይ አይደለም።
የሠራዊት አምላክ እንዲህ ይላል፦ “በመሠዊያዬ ላይ ከንቱ እሳትን ከምታቃጥሉበት ይልቅ የቤተ መቅደሱን በር የሚዘጋ ምነው ከእናንተ አንድ ሰው እንኳ በተገኘ! በእናንተ ደስ ስለማይለኝ ለእኔ የምታቀርቡትን ቊርባን አልቀበልም፤
እነሆ፥ እናንተ እየተሳለቃችሁ ‘ይህ ሁሉ ምን አሰልቺ ነገር ነው!’ ትላላችሁ። የተሰረቀውን፥ አንካሳውን ወይም የታመመውን እንስሳ ለመሥዋዕትነት ታቀርባላችሁ፤ እኔ ይህን የምቀበል ይመስላችኋልን?
ለመሆኑ የታወረውን፥ የታመመውንና አንካሳ የሆነውን እንስሳ ለመሥዋዕት ስታቀርቡ በደል የፈጸማችሁ አይመስላችሁምን? ይህን የመሰለ እንስሳ ለአለቃችሁ ገጸ በረከት አድርጋችሁ ብታቀርቡለት፥ ደስ ብሎት የሚቀበላችሁና የሚያመሰግናችሁ ይመስላችኋልን?” ይላል የሠራዊት አምላክ።
ቃላችሁን ባትጠብቁ ግን እግዚአብሔርን የምታሳዝኑ ሆናችሁ እንዳትገኙ አስጠነቅቃችኋለሁ፤ ሰለ ኃጢአታችሁም ቅጣት የሚደርስባችሁ መሆኑንም አትዘንጉ።
እንግዲህ ወንድሞቼ ሆይ! እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ፥ ሕያውና የተቀደሰ መሥዋዕት አድርጋችሁ ሁለንተናችሁን እንድታቀርቡ በመሐሪው በእግዚአብሔር ስም እለምናችኋለሁ፤ ይህም ማቅረብ የሚገባችሁ ቅንነት ያለው እውነተኛ የእግዚአብሔር አገልግሎት ነው።
ይህም ጸጋ የተሰጠኝ የእግዚአብሔርን የምሥራች ቃል ለአሕዛብ በማብሠር እንደ ካህን ሆኜ ኢየሱስ ክርስቶስን ለማገልገል ነው፤ ስለዚህ አሕዛብ በመንፈስ ቅዱስ የተቀደሰና እግዚአብሔርንም ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት ሆነው እንዲቀርቡ አገለግላለሁ።
ለአንድ ሰው አገልጋዮች ሆናችሁ ለመታዘዝ ራሳችሁን ስታቀርቡ ለዚያ ለምትታዘዙለት ሰው አገልጋዮች መሆናችሁን ታውቃላችሁ፤ እንዲሁም ለኃጢአት ብትታዘዙ ሞትን ለሚያመጣባችሁ ኃጢአት አገልጋዮች ትሆናላችሁ፤ ለእግዚአብሔር ብትታዘዙ ግን ጽድቅን ታገኛላችሁ።
ማንኛይቱም ባል የሞተባት ሴት ልጆች ወይም የልጅ ልጆች ቢኖሩአት እነዚህ ልጆች አስቀድመው ለቤተሰቦቻቸው የመጠንቀቅን፥ ለወላጆቻቸውና ለአያቶቻቸው ብድር የመመለስን መንፈሳዊ ግዴታ ይማሩ፤ ይህ እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ነገር ነው።
አቤል ከቃየል መሥዋዕት የበለጠውን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ያቀረበው በእምነት ነው፤ እግዚአብሔር የአቤልን መባ በደስታ በተቀበለ ጊዜ አቤል በእምነቱ ጻድቅ መሆኑ ተመሰከረለት፤ አቤል ቢሞትም እንኳ በእምነቱ አማካይነት አሁንም እየተናገረ ነው።
ወደ ጌታ ኢየሱስ የምትቀርቡትም እንደ ሕያዋን ድንጋዮች መንፈሳዊ ቤት ሆናችሁ ለመታነጽ ነው፤ በዚህ ዐይነት በኢየሱስ ክርስቶስ አማካይነት ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ለእግዚአብሔር ለማቅረብ ቅዱሳን ካህናት ትሆናላችሁ።