ዘፍጥረት 39:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አገልጋዮችዋን ጠርታ እንዲህ አለቻቸው፤ “እነሆ፥ ባለቤቴ ያመጣው ይህ ዕብራዊ ሊያዋርደን ነበር፤ ወዳለሁበት ክፍል ገብቶ ሊደፍረኝ ሞከረ፤ እኔ ግን ድምፄን ከፍ አድርጌ ጮኽኩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የቤት አገልጋዮቿን ጠራች፤ እንዲህም አለቻቸው፤ “አያችሁ፤ ለካስ ይህ ዕብራዊ የመጣው መሣለቂያ ሊያደርገን ኖሯል! ሊተኛኝ ወደ እኔ ገባ፤ እኔም ከፍ ባለ ድምፅ ጮኽሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የቤት አገልጋዮቿን ጠራች፤ እንዲህም አለቻቸው፤ “አያችሁ፤ ለካስ ይህ ዕብራዊ የመጣው መሣለቂያ ሊያደርገን ኖሮአል! እዚህ ድረስ ሰተት ብሎ ገብቶ ካልተኛሁሽ አለኝ፤ እኔም ጩኸቴን ለቀቅሁት፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የቤቷን ሰዎች ወደ እርስዋ ጠርታ እንዲህ ብላ ነገረቻቸው፥ “እዩ፤ ይህ ዕብራዊ ባርያ በእኛ እንዲሣለቅ አመጣብን፤ እርሱ ወደ እኔ ገብቶ ከእኔ ጋር ተኚ አለኝ፤ እኔም ድምፄን ከፍ አድርጌ ጮኽሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የቤትዋን ሰዎች ወደ እርስዋ ጠርታ እንዲህ ብላ ነገረቻቸው፦ እዮ ዕብራዊው ሰው በእኛ እንዲሣለቅ አግብቶብናል፤ እርሱ ከእኔ ጋር ሊተኛ ወደ እኔ ገባ እኔም ድምፄን ከፍ አድርጌ ጮኽሁ፤ |
ነገር ግን አንድ ሰው ሸሽቶ መጣና የሆነውን ሁሉ ለዕብራዊው ለአብራም ነገረው፤ በዚያን ጊዜ አብራም የሚኖረው በአሞራዊው መምሬ የተቀደሱ የወርካ ዛፎች አጠገብ ነበር፤ መምሬና ወንድሞቹ ኤሽኮል፥ ዐኔር የአብራም የጦር ቃል ኪዳን ጓደኞች ነበሩ።
በመጣም ጊዜ የሆነውን ታሪክ እንዲህ ስትል ዘርዝራ ነገረችው፥ “አንተ ወደዚህ ያመጣኸው ዕብራዊ አገልጋይ ወዳለሁበት ክፍል ገብቶ ሊያዋርደኝ ነበር።
እኔ ከዕብራውያን አገር ወደዚህ የመጣሁት ወድጄ ሳይሆን ተሸጬ ነው፤ እዚህም አገር ከመጣሁ ወዲህ በእስር ቤት የምገኘው ምንም በደል ሳልፈጽም ነው።”
አንቺን ለማጥፋት የሚሠራ መሣሪያ ዘላቂነት አይኖረውም፤ ለሚከሱሽ ሁሉ በቂ መልስ ይኖርሻል፤ የእኔ አገልጋዮች ርስትና ከእኔ የሚፈረድላቸው ፍርድ ይህ ነው፤” ይላል እግዚአብሔር።
እንዲህ እያሉም ይከሱት ጀመር፤ “ይህ ሰው ሕዝባችንን ሲያስት አገኘነው፤ ለሮም ንጉሠ ነገሥት ግብር እንዳይከፈል ይከለክላል፤ ደግሞ ‘እኔ ንጉሥ መሲሕ ነኝ’ እያለ ይናገራል።”
ክፉ አድርጋችሁ ቅጣት ስትቀበሉ ብትታገሡ ምን ምስጋና ይኖራችኋል? ነገር ግን መልካም አድርጋችሁ መከራ ስትቀበሉ ብትታገሡ ከእግዚአብሔር ምስጋና ታገኛላችሁ።