Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




መዝሙር 55:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ከጠላቶቼ ዛቻ የተነሣ ፈርቼአለሁ፤ በክፉዎችም ጭቈና ደቅቄአለሁ፤ እነርሱ መከራን ያመጡብኛል፤ በቊጣና በጥላቻ ይመለከቱኛል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 በጠላት ድምፅ ተሸበርሁ፤ በክፉዎች ድንፋታ ደነገጥሁ፤ መከራ አምጥተውብኛልና፤ በቍጣም ተነሣሥተው ጠላት ሆነውብኛል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ተመልከተኝ መልስም ስጠኝ፥ በኀዘኔ ተቅበዘበዝሁ ተናወጥሁም፥

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 እኔ ግን አቤቱ በአ​ንተ ታመ​ንሁ።

Ver Capítulo Copiar




መዝሙር 55:3
12 Referencias Cruzadas  

አቤሴሎም፥ “ተመልከት፤ ሕግ አንተን ይደግፍሃል፤ ነገር ግን በንጉሡ ተወክሎ ጉዳይህን በትክክል የሚያይልህ የለም” ይለዋል፤


“ንጉሥ ሆይ! ከኢየሩሳሌም ወጥተህ በሄድክበት ቀን ያደረግኹትን በደል እባክህ ይቅር በለኝ፤ ቂም በቀልም አትያዝብኝ፤ ዳግመኛም ስለ እርሱ አታስብ፤


እግዚአብሔር ግን “ችግረኞች ተጨቊነዋል፤ ስደተኞች በመከራ ብዛት ይቃትታሉ፤ ስለዚህ እነርሱ የሚፈልጉትን ደኅንነት ለመስጠት እነሣለሁ” ይላል።


ከበባ አድርገው ከሚያጠፉኝ ጨካኝ ጠላቶቼ ጠብቀኝ።


የሐሰት ምስክሮች ዐመፅን እየተናገሩ በእኔ ላይ ስለ ተነሡ ለጠላቶቼ ፍላጎት አሳልፈህ አትስጠኝ።


ክፉ ሰዎች ባልሠራሁት ወንጀል ከሰሱኝ፤ በማላውቀውም ነገር በሐሰት መሰከሩብኝ።


ሞገደኞች አደጋ ሊጥሉብኝ ተነሡ፤ ጨካኞች ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ፤ ስለ እግዚአብሔርም አያስቡም።


“እግዚአብሔር ትቶታል፤ ተከታትለን እንያዘው፤ የሚያድነው ማንም የለም” ይላሉ።


በሌሎች ሰዎች ላይ እያፌዙ የተንኰል ንግግርን ይናገራሉ፤ በትዕቢታቸውም የመጨቈን ዛቻን ይዝታሉ።


የካህናት አለቆችና የአይሁድ ሸንጎ አባሎች ሁሉ በኢየሱስ ላይ የሞት ፍርድ ለማስፈረድ የሐሰት ምስክር ይፈልጉ ነበር።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos