Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ምሳሌ 10:18 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ጥላቻውን የሚሸፍን ሰው ሐሰተኛ ነው፤ ሐሜትንም የሚያሠራጭ ሰው ሞኝ ነው።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ጥላቻውን የሚሸሽግ ሐሰተኛ አንደበት ያለው ነው፤ ሐሜትን የሚዘራ ሁሉ ሞኝ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ጥላቻን የሚከድን ሐሰተኛ ከንፈር አለው፥ ሐሜትንም የሚገልጥ አላዋቂ ነው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ልዝብ ከንፈሮች ጥልን ይሸፍናሉ፤ ስድብን የሚያወጡ ግን ሰነፎች ናቸው።

Ver Capítulo Copiar




ምሳሌ 10:18
18 Referencias Cruzadas  

ንግግሩ እንደ ቅቤ የለዘበ ነው፤ በልቡ የሚያስበው ግን ጦርነትን ነበር አንደበቱ ከዘይት ይበልጥ የለሰለሰ ነው፤ ነገር ግን እንደ ተመዘዘ ሰይፍ ነው።


ሌሎች ሰዎችን የማያማ፥ በጓደኞቹ ላይ ክፉ ነገር የማያደርግ፥ በጐረቤቱ ላይ አሉባልታን የማያሠራጭ፥


አበኔር ወደ ኬብሮን በደረሰ ጊዜ ኢዮአብ በግል ሊያነጋግረው የፈለገ በመምሰል ወደ ቅጽሩ በር ገለል አድርጎ ወሰደው፤ እዚያም ሆዱን ወግቶ ገደለው፤ ኢዮአብ ይህን ያደረገበት ምክንያት አበኔር ቀደም ብሎ ወንድሙን ዐሣሄልን ስለ ገደለበት ለመበቀል ነው።


ሰውን በሹክሹክታ የሚያማውን ሰው ዝም አሰኛለሁ፤ ትዕቢተኛ ዐይንና ትምክሕተኛ ልብ ያለውን ሰው አልታገሠውም።


በወንድምህ ላይ ሁልጊዜ ክፉ ነገር ትናገራለህ፤ የእናትህንም ልጅ ታማለህ።


አንዱ ለአንዱ ውሸትን ይናገራል፤ በሚያቈላምጥ አንደበት የሚናገሩትም በሁለት ልብ ነው።


ጠላቶቼ የሚናገሩት ሁሉ ከእውነት የራቀ ስለ ሆነ፥ ከአፋቸው እውነት አይገኝም፤ ሐሳባቸውም በተንኰል የተሞላ ነው፤ ጒሮሮአቸውም እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፤ በምላሳቸውም ሰውን ይሸነግላሉ።


ስለዚህም ሳኦል ዳዊትን ይበልጥ ከመፍራቱ የተነሣ በኖረበት ዘመን ሁሉ የዳዊት ጠላት ሆነ።


“ሐሰተኛ ወሬ አታሠራጭ፤ በሐሰት በመመስከርም ከወንጀለኛ ሰው ጋር አትተባበር፤


እያንዳንዱ ከባልንጀራው ተንኰል ይጠንቀቅ፤ ወንድሙን እንኳ ቢሆን ማመን የለበትም፤ ወንድም የተባለ ሁሉ (እንደ ያዕቆብ) አታላይ ሆኖአል፤ ወዳጅ የተባለም ሁሉ የባልንጀራውን ስም ያጠፋል።


በሕዝብህ መካከል እየዞርክ የስም አጥፊነት ወሬ አታሰራጭ፤ ሰውን ወደ ሞት አደጋ የሚያደርስ ምንም ነገር አታድርግ፤ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ነኝ።


ሁሉም እንደ ነሐስና እንደ ብረት የጠነከሩ፤ በእልህም የተወጠሩ ዐመፀኞች ናቸው። ሁሉም የተበላሹ የሐሜት ሱሰኞች ናቸው፤


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios