ይኸውም እኔ በመካከላቸው ከምኖረው ከከነዓናውያን ሴቶች ልጆች መካከል ለልጄ ሚስት እንዳትመርጥ በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር ስም ማልልኝ፤
ዘፍጥረት 38:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እዚያም ይሁዳ የከነዓናዊውን የሹዓን ሴት ልጅ አየ፤ እርስዋንም አግብቶ ወደርስዋ ገባ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እዚያም ሳለ፣ ይሁዳ የከነዓናዊውን የሹዓን ሴት ልጅ አየ፤ እርሷንም አግብቶ ዐብሯት ተኛ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እዚያም ሳለ፥ ይሁዳ የከነዓናዊውን የሴዋን ሴት ልጅ አየ፤ እርሷንም አግብቶ አብሯት ተኛ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚያም ይሁዳ ያንድ ከነዓናዊ ሰው ሴት ልጅን አየ፤ ስምዋም ሴዋ ይባላል። ወሰዳትም፤ ወደ እርስዋም ገባ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዚያም ይሁዳ የከነዓናዊውን የሴዋን ሴት ልጅ አየ ወሰዳትም ወደ እርስዋም ገባ። |
ይኸውም እኔ በመካከላቸው ከምኖረው ከከነዓናውያን ሴቶች ልጆች መካከል ለልጄ ሚስት እንዳትመርጥ በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር ስም ማልልኝ፤
ሴቲቱም ዛፉ የሚያምር፥ ፍሬውም ለመብላት የሚያስጐመዥና ጥበብን የሚያስገኝ እንደ ሆነ ባየች ጊዜ ከፍሬው ወስዳ በላች፤ ለባሏም ከፍሬው ሰጠችው፤ እርሱም በላ።
የይሁዳ ልጆች፦ ዔር፥ ኦናን፥ ሴላ፥ ፋሬስና ዛራሕ ናቸው፤ ዔርና ኦናን ግን በከነዓን ምድር ሞተዋል። የፋሬስ ልጆች ሔጽሮንና ሐሙል ናቸው።
በዚያን ዘመንና ከዚያም በኋላ ከሰዎች ሴቶች ልጆችና ከእግዚአብሔር ልጆች ተዳቅለው የተወለዱ “ኔፊሊም” የሚባሉ ግዙፎች ሰዎች ነበሩ። እነርሱ በጥንት ዘመን በጀግንነታቸው የታወቁ ዝነኞች ሰዎች ነበሩ።
አንድ ቀን ከቀትር በኋላ ዘግየት ብሎ ዳዊት ከቀን እንቅልፉ ነቅቶ ወደ ቤተ መንግሥቱ ሰገነት ወጣ፤ እዚያም ወዲያና ወዲህ ሲመላለስ ገላዋን የምትታጠብ አንዲት ሴት አየ፤ ሴትዮዋም በጣም ውብ ነበረች፤
ይሁዳ ከከነዓናዊት ሚስቱ ከባትሹዓ ዔር፥ ኦናንና ሼላ ተብለው የሚጠሩ ሦስት ወንዶች ልጆችን ወለደ፤ የበኲር ልጁ ዔር በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ሰው ስለ ነበር እግዚአብሔር በሞት ስለ ቀሠፈው፥
ወደ ቤቱም ተመልሶ ለአባቱና ለእናቱ “በቲምና ከፍልስጥኤማውያን ሴቶች ልጆች አንድዋን አይቼ ወድጃታለሁ፤ ስለዚህ እርስዋን አጭታችሁ አጋቡኝ” አላቸው።
አንድ ቀን ሶምሶን የፍልስጥኤማውያን ከተማ ወደሆነችው ወደ ጋዛ ሄደ፤ እዚያም አንዲት አመንዝራ ሴት አይቶ ከእርስዋ ጋር ለማደር ወደ ቤትዋ ገባ፤