ዘፍጥረት 36:34 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮባብም በሞተ ጊዜ የቴማን አገር ተወላጅ ሑሻም በእርሱ እግር ተተክቶ ነገሠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮባብ ሲሞት፣ የቴማን አገር ሰው ሑሳም በምትኩ ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮባብም ሞተ፥ በስፍራውም የቴማኒው አገር ሑሻም ነገሠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮባብም ሞተ፤ በእርሱም ፈንታ የቴማኒው ሀገር ሑሳም ነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በስፍራውም የቴማኒው አገር ሑሳም ነገሠ |
ሑሻምም በሞተ ጊዜ የምድያምን ሰዎች በሞአብ ሜዳ ድል የመታው የበዳድ ልጅ ሀዳድ በእርሱ ተተክቶ ነገሠ፤ የነገሠባትም ከተማ ዐዊት ትባል ነበር።
የቴማን አገር ሰው የሆነው ኤሊፋዝ፥ የሹሐ አገር ሰው የሆነው ቢልዳድና የናዕማ አገር ሰው የሆነው ጾፋር፥ እነዚህ ሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች ነበሩ። እነርሱም በኢዮብ ላይ የደረሰውን ሥቃይ በሰሙ ጊዜ ሐዘናቸውን ሊገልጹለትና ሊያጽናኑት ከየአገራቸው ተጠራርተው በአንድነት ወደ ኢዮብ መጡ።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ስለ ኤዶም የተናገረው ይህ ነው፦ “የቴማን ከተማ ሕዝብ ከዚህ በፊት የነበራቸውን ጥበብ አጥተዋልን? አማካሪዎቻቸውስ ምክር መስጠት አቅቷቸዋልን? የነበራቸውስ ጥበብ የት ደረሰ?
ስለዚህ አሁን ኤዶምን እንደምቀጣና በዚያም ያሉትን ሰዎችና እንስሶች በሙሉ እንደማጠፋ አሳውቃለሁ፤ ከቴማን ከተማ እስከ ደዳን ከተማ ድረስ ባድማ እንዲሆን አደርጋለሁ፤ ሕዝቡም በጦርነት ያልቃሉ፤