ከዚህ በኋላ ሎጥ ሴቶች ልጆቹን ወዳጩአቸው ሰዎች ቤት ሄደና “ቶሎ ብላችሁ ከዚህ ውጡ፤ እግዚአብሔር ይህን ስፍራ ሊደመስሰው ነው” አላቸው፤ እነርሱ ግን የሚቀልድ መስሎአቸው ቸል አሉ።
ዘፍጥረት 34:9 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲያውም በመካከላችን የጋብቻ ውል እናድርግ፤ እኛ የእናንተን ሴቶች ልጆች እናግባ፤ እናንተም የእኛን ሴቶች ልጆች አግቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጋብቻ እንተሳሰር፤ ሴት ልጃችሁን ስጡን፤ የእኛንም ሴቶች አግቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእኛም ጋር በጋብቻ ተሳሰሩ፥ ሴቶች ልጆቻችሁን ስጡን፥ እናንተም የእኛን ሴቶች ልጆች ውሰዱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጋብቾችም ሁኑን፤ ሴቶች ልጆቻችሁን ስጡን፤ እናንተም የእኛን ሴቶች ልጆች ለልጆቻችሁ ውሰዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጋብቾችም ሁኑን፤ ሴቶች ልጆች ስጡን እናንተም የእኛን ሴቶች ልጆች ውሰዱ። |
ከዚህ በኋላ ሎጥ ሴቶች ልጆቹን ወዳጩአቸው ሰዎች ቤት ሄደና “ቶሎ ብላችሁ ከዚህ ውጡ፤ እግዚአብሔር ይህን ስፍራ ሊደመስሰው ነው” አላቸው፤ እነርሱ ግን የሚቀልድ መስሎአቸው ቸል አሉ።
ይኸውም እኔ በመካከላቸው ከምኖረው ከከነዓናውያን ሴቶች ልጆች መካከል ለልጄ ሚስት እንዳትመርጥ በሰማይና በምድር አምላክ በእግዚአብሔር ስም ማልልኝ፤
ርብቃ ይስሐቅን “ዔሳው ባገባቸው በእነዚህ በሒታውያን ሴቶች ምክንያት መኖሬን ጠላሁት፤ ያዕቆብ ደግሞ ከነዚህ ከሒታውያን ሴቶች አንዲቱን ካገባ ከመኖር ይልቅ ሞቴን እመርጣለሁ” አለችው።
በዚህ ዐይነት በአገራችን ላይ ከእኛ ጋር መኖር ትችላላችሁ፤ በፈለጋችሁበት ስፍራ በመዘዋወር እየሠራችሁና እየነገዳችሁ ርስትም ይዛችሁ መኖር ትችላላችሁ።”
ታዲያ እንዴት እንደገና የአንተን ትእዛዞች ጥሰን ከእነዚህ ዐመፀኞች ሕዝቦች ጋር ጋብቻ እንፈጽማለን? በዚህስ ምክንያት ምንም ቅሬታ ሳታስቀርልን እኛን በቊጣህ አታጠፋንምን?