አጋርም “በእርግጥ የሚያየኝን እግዚአብሔርን በዐይኔ አይቼ በሕይወት ኖርሁን?” በማለት ያነጋገራትን ጌታ “ኤልሮኢ” አለችው፤ ትርጒሙም “የሚያየኝ አምላክ” ማለት ነው።
ዘፍጥረት 32:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብ ከጵንኤል ተነሥቶ ሲሄድ ፀሐይ ወጥታ ነበር፤ በጭኑም ሕመም ምክንያት ያነክስ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጵኒኤልንም እንዳለፈ ፀሓይ ወጣችበት፤ እርሱም በጭኑ ምክንያት ያነክስ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጵኒኤልንም ሲያልፍ ፀሐይ ወጣችበት፥ እርሱም በጭኑ ምክንያት ያነክስ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ራእየ እግዚአብሔርንም በተወ ጊዜ ፀሐይ ወጣችበት። እርሱም በጭኑ ምክንያት ያነክስ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዽኒኤልንም ሲያልፍ ፀሐይ ወጣችበት፥ እርሱም በጭኑ ምክንያት ያነክስ ነበር። |
አጋርም “በእርግጥ የሚያየኝን እግዚአብሔርን በዐይኔ አይቼ በሕይወት ኖርሁን?” በማለት ያነጋገራትን ጌታ “ኤልሮኢ” አለችው፤ ትርጒሙም “የሚያየኝ አምላክ” ማለት ነው።
በማግስቱ ጠዋት በማለዳ መላእክቱ ሎጥን “ፍጠን! ከተማይቱ ስትጠፋ አብራችሁ እንዳትጠፉ ሚስትህንና ሁለቱን ሴቶች ልጆችህን ይዘህ ከዚህ ውጣ” እያሉ አጣደፉት።
ያዕቆብ ከሰውየው ጋር ሲታገል ሰውየው ሹልዳውን መቶት ስለ ነበር እስራኤላውያን እስከ ዛሬ ድረስ በጭን መጋጠሚያ ላይ ያለውን የሹልዳ ሥጋ አይበሉም።
የእስራኤል ንጉሥ ኢዮርብዓም በኮረብታማው በኤፍሬም አገር የምትገኘውን የሴኬምን ከተማ ምሽግ አድርጎ በዚያ ለጥቂት ጊዜ ቈየ፤ ከዚያም በመነሣት የፐኑኤልን ከተማ ምሽግ አድርጎ ሠራ፤
እነርሱም የመጣላቸውን ኰርማ ወስደው ለመሥዋዕት አዘጋጅተው እስከ እኩለ ቀን ድረስ ወደ ባዓል ጸለዩ። “ባዓል ሆይ! እባክህ ስማን!” እያሉም ጮኹ። በሠሩትም መሠዊያ እየዘለሉ ዞሩ፤ ነገር ግን ምንም መልስ አላገኙም።
እኔም “እነሆ አንደበቶቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል የምኖር፥ አንደበቴም የረከሰብኝ ሰው ነኝ፤ ንጉሡን የሠራዊት አምላክን በዐይኖቼ አይቼአለሁና መጥፋቴ ስለ ሆነ ወዮልኝ!” አልኩ።
ከነዚህ ከተገለጡልኝ ታላላቅ ነገሮች የተነሣ እንዳልታበይ ሥጋዬን እንደ እሾኽ የሚወጋ ሥቃይ ተሰጠኝ፤ ይህም የሰይጣን መልእክተኛ በመሆን እየጐሸመ በማሠቃየት እንዳልታበይ ያደርገኛል።
ነገር ግን እርሱ “የእኔ ኀይል ፍጹም ሆኖ የሚገለጠው በአንተ ደካማነት ስለ ሆነ ጸጋዬ ይበቃሃል” አለኝ፤ ስለዚህ የክርስቶስ ኀይል በእኔ ላይ እንዲሆን ከምን ጊዜውም ይልቅ በደካማነቴ ደስ እያለኝ ልመካ እወዳለሁ።
እንዲህ አላችሁ፦ ‘በእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገር በሰማነው ጊዜ እግዚአብሔር አምላካችን ታላቅነቱንና ክብሩን በግልጥ አሳይቶናል፤ እግዚአብሔር ካነጋገረው በኋላ እንኳ ሰው በሕይወት መኖር እንደሚችል በዛሬው ዕለት አይተናል።
ጌዴዎን ያየው የእግዚአብሔር መልአክ መሆኑን በተገነዘበ ጊዜ “ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! የአንተን መልአክ ፊት ለፊት አይቼአለሁ ወዮልኝ!” አለ።
ጌዴዎን ወደ ጵኑኤልም ሄዶ በዚያ የሚኖሩትን ሰዎች ያንኑ ጥያቄ አቀረበላቸው፤ ነገር ግን የጵኑኤልም ሰዎች የሱኮት ሰዎች የሰጡትን ተመሳሳይ መልስ ሰጡት።