ዘፍጥረት 32:29 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብም “አንተስ ስምህ ማን ነው?” አለው። ሰውየውም “ስሜን ለማወቅ የምትፈልገው ለምንድን ነው?” አለውና ያዕቆብን ባረከው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብም፣ “እባክህ ስምህን ንገረኝ” ብሎ ጠየቀው። ሰውየውም፣ “ስሜን ለማወቅ ለምን ፈለግህ?” አለው፤ በዚያም ስፍራ ባረከው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብም፦ “ልለምንህ፥ ስምህን ንገረኝ” ብሎ ጠየቀው። እርሱም፦ “ስሜን ለምን ትጠይቃለህ?” አለው። በዚያም ስፍራ ባረከው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብም፥ “ስምህን ንገረኝ” ብሎ ጠየቀው። እርሱም፥ “ስሜን ለምን ትጠይቃለህ? ድንቅ ነውና” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብም፦ ስምህን ንገረኝ ብሎ ጠየቀው። እርሱም፦ ስሜን ለምን ትጠይቃለህ? አለው። በዚያም ስፍራ ባረከው። |
ደግሞም “ስምህ ያዕቆብ ነው፤ ከእንግዲህ ወዲህ ግን እስራኤል ትባላለህ እንጂ ያዕቆብ ተብለህ አትጠራም” አለው። ስለዚህም እግዚአብሔር ያዕቆብን “እስራኤል” ብሎ ጠራው።
ይህንኑ አሮጌ ልማዳቸውን እስከ አሁን ድረስ በመፈጸም ላይ ናቸው፤ እነርሱ እግዚአብሔርን አያመልኩም፤ ወይም ስሙ እስራኤል ተብሎ ለተጠራው ለያዕቆብ ልጆች እግዚአብሔር በሰጣቸው ደንቦች፥ ሥርዓቶች፥ ሕጎችና ትእዛዞች ጸንተው አልኖሩም።
ወደ ሰማይ ወጥቶ የወረደ ማን ነው? ነፋስን በእጁ የጨበጠ፥ ውሃን በልብሱ የቋጠረ፥ የምድርን ዳርቻ ያጸና ማን ነው? የሰውዬው ስም ማነው? የልጁስ ስም ማን ይባላል? ታውቅ እንደሆን ንገረኝ፤
እነሆ ሕፃን ተወልዶልናል! ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል! እርሱም መሪ ይሆናል፤ ስሙም “ድንቅ መካር፥ ኀያል አምላክ፥ የዘለዓለም አባት፥ የሰላም አለቃ” ይባላል።
ሙሴ ለኤዶም ንጉሥ እንዲህ ብለው እንዲነግሩት መልእክተኞችን ከቃዴስ ላከ፤ “ወንድምህ እስራኤል እንዲህ ይላል፦ በእኛ ላይ የደረሰውን ችግር ሁሉ ሰምተሃል፤
መልአኩም እንዲህ ሲል መለሰለት፦ “እኔ በእግዚአብሔር ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፤ ይህን የምሥራች እንድነግርህ ከእግዚአብሔር ዘንድ ተልኬ መጥቻለሁ።
“እግዚአብሔር አምላካችን ምሥጢር ያደረጋቸው ብዙ ነገሮች አሉ፤ የተገለጡ ነገሮች ግን እኛና ልጆቻችን ልንጠብቃቸው የሚገባን የሕጉ ቃሎች ሁሉ ናቸው።