ዘፍጥረት 31:46 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቤተሰቡንም ሁሉ “ድንጋይ ሰብስቡ” አላቸው፤ ድንጋይ ሰብስበው ከቈለሉ በኋላም በአጠገቡ ተቀምጠው ምግብ ተመገቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ያዕቆብ ዘመዶቹን፣ “ድንጋይ ሰብስቡ” አላቸው። እነርሱም ድንጋይ እያመጡ ከመሩ፤ በክምሩም አጠገብ ምግብ በሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብም ዘመዶቹን “ድንጋይ ሰብስቡ” አላቸው፥ እነርሱም ድንጋይ ሰብስበው ከመሩ፥ በድንጋዩም ክምር ላይ በሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብም ወንድሞቹን፥ “ድንጋይ ሰብስቡ” አላቸው፤ እነርሱም ድንጋይ ሰብስበው ከመሩ፤ በድንጋዩም ክምር ላይ በሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብም ወንድሞቹን ድንጋይ ሰብስቡ አላቸው እነርሱም ድንጋይ ስብስበው ከመሩ፤ በድንጋዩም ክምር ላይ በሉ። |
ከእኛ መካከል የአንተ ጣዖቶች የተገኙበት ሰው ቢኖር ግን ይሙት፤ እነሆ፥ አሁን ዘመዶቻችንን ምስክር በማድረግ የአንተ የሆነውን ነገር ሁሉ ፈልገህ ውሰድ” አለው፤ ያዕቆብ ይህን ያለው ራሔል የአባቷን ጣዖቶች ሰርቃ እንደ ወሰደች ስላላወቀ ነው።
ዕቃዬን ሁሉ ከበረበርክ በኋላ የአንተ የሆነ ነገር ምን አግኝተሃል? አንዳች ነገር አግኝተህ ቢሆን በአንተና በእኔ ዘመዶች ፊት እዚህ አቅርበው፤ እነርሱም ከአንተና ከእኔ አጥፊው ማን እንደሆን ይፍረዱ።
የአቤሴሎምንም ሬሳ ወስደው በደን ውስጥ በሚገኘው ጥልቅ ጒድጓድ ውስጥ ጣሉት፤ በእርሱም ላይ ብዙ ትልልቅ ድንጋይ ከምረው እንዲሸፈን አደረጉት፤ እስራኤላውያንም ሁሉ ሸሽተው እያንዳንዱ ሰው ወደየቤቱ ገባ።
በእርሱም ላይ እስከ ዛሬ ድረስ የሚታይ ታላቅ የድንጋይ ክምር ከመሩበት፤ እግዚአብሔርም ከቊጣው ተመለሰ፤ ስለዚህም ያ ቦታ የአኮር ሸለቆ ተብሎ ይጠራል።