Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 31:37 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

37 ዕቃዬን ሁሉ ከበረበርክ በኋላ የአንተ የሆነ ነገር ምን አግኝተሃል? አንዳች ነገር አግኝተህ ቢሆን በአንተና በእኔ ዘመዶች ፊት እዚህ አቅርበው፤ እነርሱም ከአንተና ከእኔ አጥፊው ማን እንደሆን ይፍረዱ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

37 ዕቃዬን አንድ በአንድ በርብረሃል፤ ታዲያ፣ የአንተ ሆኖ ያገኘኸው ዕቃ የትኛው ነው? ካለ፣ እስኪ በአንተም በእኔም ዘመዶች ፊት አቅርብና እነርሱ ያፋርዱን።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

37 አሁንም ዕቃዬን ሁሉ በረበርህ፥ የቤትህስ ሁሉ የሆነ ዕቃ ምን አገኘህ? እነርሱ በእኛ በሁለታችን መካከል ይፈርዱ ዘንድ በዘመዶቼና በዘመዶችህ ፊት አቅርበው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

37 አሁ​ንም ዕቃ​ዬን ሁሉ በረ​በ​ርህ፤ ከቤ​ት​ህስ ዕቃ ሁሉ ምን አገ​ኘህ? እነ​ርሱ በእኛ በሁ​ለ​ታ​ችን መካ​ከል ይፈ​ርዱ ዘንድ በወ​ን​ድ​ሞ​ችና በወ​ን​ድ​ሞ​ችህ ፊት አቅ​ር​በው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

37 አሁንም ዕቃዬን ሁሉ በረበርህ ከቤትህስ ዕቃ ሁሉ ምን አገኘህ? እነርሱ በእኛ በሁለታችን መካከል ይፈርዱ ዘንድ በወንድሞቼና በወንድሞችህ ፊት አቅርበው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 31:37
11 Referencias Cruzadas  

ከእኛ መካከል የአንተ ጣዖቶች የተገኙበት ሰው ቢኖር ግን ይሙት፤ እነሆ፥ አሁን ዘመዶቻችንን ምስክር በማድረግ የአንተ የሆነውን ነገር ሁሉ ፈልገህ ውሰድ” አለው፤ ያዕቆብ ይህን ያለው ራሔል የአባቷን ጣዖቶች ሰርቃ እንደ ወሰደች ስላላወቀ ነው።


በዚህ ጊዜ ያዕቆብ እንዲህ ሲል ላባን በቊጣ ቃል ተናገረው፤ “ታዲያ፥ የፈጸምኩት በደል ምንድን ነው? እስቲ ምን አጥፍቼ ነው እንዲህ የምታሳድደኝ?


ከአንተ ጋር መኖር ከጀመርኩ ኻያ ዓመት ሆነኝ፤ በዚህ ጊዜ ውስጥ በጎችህና ፍየሎችህ የጨነገፉበት ጊዜ የለም፤ ከመንጋህም አንድ ጠቦት እንኳ በልቼ አላውቅም፤


ባይሰማህ ግን የሁለት ወይም የሦስት ሰዎች ምስክርነት ስለሚጸና ሁለት ወይም ሦስት ሰዎች ይዘህ ወደ እርሱ ሂድ።


በእናንተ በአማኞች መካከል በነበርንበት ጊዜ እንዴት ባለ ቅድስናና ጽድቅ ነቀፋም በሌለበት ሕይወት እንደ ኖርን እናንተ ምስክሮች ናችሁ፤ እግዚአብሔርም ምስክር ነው፤


ጸልዩልን፤ ንጹሕ ኅሊና እንዳለን እርግጠኞች ነን፤ በሁሉም መንገድ በመልካም ጠባይ ለመኖር እንመኛለን፤


እነርሱንም ከድንኳኑ በማውጣት፥ ወደ ኢያሱና ወደ እስራኤላውያን አምጥተው በእግዚአብሔር ፊት አኖሩአቸው።


ምናልባት “ክፉ አድራጊዎች ናቸው” ብለው ቢያሙአችሁም እንኳ እግዚአብሔር እኛን ለመጐብኘት በሚመጣበት ቀን አሕዛብ መልካም ሥራችሁን አይተው እግዚአብሔርን እንዲያመሰግኑ በእነርሱ መካከል ስትኖሩ መልካም ጠባይ ይኑራችሁ።


መልሳችሁ ግን በገርነትና በአክብሮት ይሁን፤ የክርስቶስ በመሆናችሁ ባላችሁ መልካም ጠባይ ላይ ክፉ የሚናገሩ ሰዎች በክፉ ንግግራቸው እንዲያፍሩ መልካም ኅሊና ይኑራችሁ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos