እግዚአብሔርም በሕልም እንዲህ አለው፦ “በንጹሕ ኅሊና እንዳደረግህ ዐውቄአለሁ፤ ወደ እርስዋ ቀርበህ በእኔ ፊት ኃጢአት እንዳትሠራ ያደረግኩህም ስለዚህ ነው።
ዘፍጥረት 31:10 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እንስሶቹ ለመፅነስ ፍትወት በሚያድርባቸው ወራት የሚያጠቁአቸው አውራ ፍየሎች ሽመልመሌ፥ ዝንጒርጒርና ነቊጣ መሆናቸውን በሕልም አየሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እንስሳቱ በሚጠቁበት ወራት፣ የሚያጠቋቸው አውራ ፍየሎች መልካቸው፣ ሽመልመሌ፣ ዝንጕርጕርና ነቍጣ ያለባቸው መሆናቸውን ዐይኔን አንሥቼ በሕልሜ አየሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በመንጋዎቹ መራቢያ ወራት ዐይኖቼን አነሳሁ፥ በሕልምም በበጎቹ ላይ የሚንጠላጠሉት አውራ ፍየሎች ሽመልመሌ፥ ዝንጉርጉርና ነቊጣ እንደ ነበሩ አየሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ሆነ፤ በጎቹ በሚፀንሱ ጊዜ ዐይኔን አንሥቼ በሕልም አየሁ፤ እነሆም፥ በበጎችና በፍየሎች ላይ የሚንጠላጠሉት የበጎችና የፍየሎች አውራዎች ነጭ፥ ዝንጕርጕሮችና ሐመደ ክቦ ነበሩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ሆነ በጎቹ በጎመጁ ጊዜ ዓይኔን አንሥቼ በሕልም አየሁ እነሆም በበጎችና በፍየሎች ላይ የሚንጠላጠሉት የበጎችን የፍየሎች አውራዎች ሽመልመሌ መሳዮችና ዝንጕርጕሮች ነቁጣ ያለባቸውም ነበሩ። |
እግዚአብሔርም በሕልም እንዲህ አለው፦ “በንጹሕ ኅሊና እንዳደረግህ ዐውቄአለሁ፤ ወደ እርስዋ ቀርበህ በእኔ ፊት ኃጢአት እንዳትሠራ ያደረግኩህም ስለዚህ ነው።
እርሱም እንዲህ አለኝ፤ ‘መንጋዎቹን የሚያጠቁአቸው አውራ ፍየሎች ሽመልመሌ፥ ዝንጒርጒርና ነቊጣ ያለባቸው መሆናቸውን ተመልከት፤ ላባ የፈጸመብህን በደል ስላየሁ ይህን ያደረግኹት እኔ ነኝ፤
እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ “እነሆ፥ እኔ የምነግራችሁን አድምጡ! በመካከላችሁ ነቢያት ቢኖሩ ራሴን የምገልጥላቸው በራእይ ነው፤ በሕልምም አነጋግራቸዋለሁ፤