ዘፍጥረት 30:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ራሔልም “እግዚአብሔር ፈረደልኝ፤ ጸሎቴንም ሰምቶ ወንድ ልጅ ሰጠኝ” አለች፤ በዚህም ምክንያት ስሙን ዳን ብላ ጠራችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ራሔልም፣ “እግዚአብሔር ፈርዶልኛል፣ ልመናዬንም ሰምቶ ወንድ ልጅ ሰጥቶኛል” አለች። ስለዚህ ስሙን ዳን ብላ አወጣችለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ራሔልም፦ እግዚአብሔር ፈረደልኝ፥ ቃሌንም ደግሞ ሰማ፥ ወንድ ልጅንም ሰጠኝ አለች፥ ስለዚህ ስሙን ዳን ብላ ጠራችው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ራሔልም፥ “እግዚአብሔር ፈረደልኝ፤ ቃሌንም ደግሞ ሰማ፤ ወንድ ልጅንም ሰጠኝ” አለች፤ ስለዚህ ስሙን ዳን ብላ ጠራችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ራሔልም፦ እግዚአብሔር ፈረደልኝ፥ ቃሌንም ደግሞ ሰማ፥ ወንድ ልጅንም ስጠኝ አለች፤ ስለዚህ ስሙን ዳን ብላ ጠራችው። |
የዳን ልጆች፥ በየትውልዳቸው፥ በየወገናቸውና በየአባቶቻቸው ቤቶች እንደየስማቸው ቊጥር ኻያ ዓመትና ከዚያም በላይ የሆኑ ወንዶች ሁሉ ተቈጠሩ፤