ዘፍጥረት 27:12 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምናልባት አባቴ ቢዳስሰኝና እንዳታለልኩት ቢያውቅ በምርቃት ፈንታ ርግማን እንደማተርፍ ታውቂ የለምን?” አላት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታዲያ፣ አባቴ ቢዳስሰኝ እንዳታለልሁት ያውቃል፤ ይህ ከሆነ ደግሞ፣ በምርቃት ፈንታ ርግማን አተርፋለሁ ማለት ነው።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምናልባት አባቴ ቢዳስሰኝ በፊቱ እንደሚዘብት እሆናለሁ፥ መርገምንም በላዬ አመጣለሁ፥ በረከትን አይደለም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ምናልባት አባቴ ቢዳስሰኝ በፊቱ እንደምንቀው እሆናለሁ፤ መርገምን በላዬ አመጣለሁ፤ በረከትንም አይደለም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በፊቱ እንደሚዘብት እሆናለሁ መርገምንም በላዬ አመጣለሂ በረከትን አይደለም። |
ዔሳውም “እርሱ እኔን ሲያሰናክለኝ ይህ ሁለተኛው ነው፤ ያዕቆብ መባሉ ተገቢ ነው፤ ከዚህ በፊት ብኲርናዬን ወሰደብኝ፤ አሁን ደግሞ ምርቃቴን ቀማኝ፤ ታዲያ፥ ለእኔ ያስቀረኸው ምንም ምርቃት የለምን?” አለው።
ቸል በማለት የእግዚአብሔርን ሥራ ከልብ የማይፈጽም ሰው የተረገመ ይሁን! እግዚአብሔር በሚያዘውም ጊዜ ሰይፉን ከደም የሚከለክል የተረገመ ይሁን!
እኔ ታላቅ ንጉሥ ነኝ፤ ስሜም በሕዝቦች ዘንድ የተከበረስለሆነ፥ ከበግ መንጋዎቹ መካከል አውራ በግ እያለው ለተሳለው ስለት ነውር ያለበትን በግ መሥዋዕት የሚያቀርብልኝ የተረገመ ነው!” ይላል የሠራዊት አምላክ።