ዘፍጥረት 26:14 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብዙ የበግና የከብት መንጋ፥ እንዲሁም ብዙ አገልጋዮች ስለ ነበሩት ፍልስጥኤማውያን ቀኑበት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ብዙ የበግና የፍየል መንጋ፣ ብዙ ከብት፣ ብዙ አገልጋዮችም ስለ ነበሩት፣ ፍልስጥኤማውያን ተመቀኙት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በግና ላም ከብትም ሎሌዎችም እጅግ በዙለት፥ የፍልስጥኤም ሰዎች ቀኑበት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮችን፥ ብዙ በጎችንና ላሞችን፥ የእርሻ መሬትንም ገዛ፤ የፍልስጥኤም ሰዎችም ቀኑበት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የበግና የላም ከብትም ሎሌዎችም እጅግ በዙለት የፍልስጥኤም ሰዎች ቀኑበት። |
እግዚአብሔር ጌታዬን እጅግ ባርኮታል፤ ባለጸጋም አድርጎታል፤ ብዙ የበግ፥ የፍየልና የከብት መንጋ፥ ብርና ወርቅ፥ ወንዶችና ሴቶች አገልጋዮች ግመሎችና አህዮች ሰጥቶታል።
በሀብትም በኩል ሰባት ሺህ በጎች፥ ሦስት ሺህ ግመሎች፥ አምስት መቶ ጥማድ በሬዎችና አምስት መቶ አህዮች ነበሩት፤ እንዲሁም እጅግ ብዙ አገልጋዮች ነበሩት፤ በምሥራቅ አገር ካሉት ሰዎች ሁሉ እርሱን የሚያኽል ሀብታምና ታላቅ ሰው አልነበረም።
እግዚአብሔር የኢዮብን የመጨረሻ ሕይወት ከመጀመሪያው አስበልጦ ባረከው፤ ስለዚህ ኢዮብ ዐሥራ አራት ሺህ በጎች፤ ስድስት ሺህ ግመሎች፤ አንድ ሺህ ጥማድ በሬዎች፤ አንድ ሺህ እንስት አህዮች ነበሩት።
ደግሞም ሰዎች የተመኙትን ለማግኘት ተግተው በመሥራት ምን ያኽል እንደሚደክሙ ተመለከትኩ፤ ይህንንም የሚያደርጉት በባልንጀሮቻቸው ላይ በመቅናት መሆኑን ተረዳሁ፤ ይህም ሁሉ ከንቱ ስለ ሆነ ነፋስን ለመጨበጥ እንደ መሞከር ነው።