ዘፍጥረት 24:4 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ወደ ትውልድ አገሬ ሂድ፤ እዚያም ካሉት ወገኖቼ መካከል ለልጄ ለይስሐቅ ሚስት ምረጥለት።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገር ግን ወደ አገሬ፣ ወደ ገዛ ዘመዶቼ ሄደህ ለልጄ ለይሥሐቅ ሚስት ትፈልግለታለህ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገር ግን ወደ አገሬና ወደ ተወላጆቼ ትሄዳለህ፥ ለልጄ ለይስሐቅም ሚስትን ትወስድለታለህ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ወደ ተወለድሁበት ወደ ሀገሬና ወደ ተወላጆች ሂድ፤ ለልጄ ለይስሐቅም ከዚያ ሚስትን አምጣለት።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ወደ አገሬና ወደ ተወላጆቼ ትሄዳለህ፥ ለልጄ ለይስሐቅም ሚስትን ትወስድለታለህ። |
እግዚአብሔር ለአብራም ተገለጠለትና “ለዘርህ የምሰጠው ምድር ይህ ነው” አለው፤ ከዚህ በኋላ አብራም ለተገለጠለት አምላክ በዚያ ቦታ መሠዊያ ሠራ።
አገልጋዩም “ምናልባት የምመርጥለት ሴት ከእኔ ጋር ወደዚህ አገር ለመምጣት እምቢ ብትልስ? ልጅህን ቀድሞ አንተ ወደነበርክበት አገር እንዲመለስ ላድርገውን?” ብሎ ጠየቀ።
አባቱና እናቱ ግን “ሚስት ለማግኘት ወደ አልተገረዙ ፍልስጥኤማውያን ዘንድ ሄደህ ሚስት የምትፈልገው ከወገንህ ወይም በሕዝባችን መካከል ሴት ልጅ የሌለች ሆኖ ነውን?” ሲሉ ጠየቁት። ሶምሶን ግን አባቱን “እኔ እርስዋን በጣም ስለ ወደድኳት ከእርስዋ ጋር አጋባኝ” አለው።