Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘፍጥረት 24:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 አገልጋዩም “ምናልባት የምመርጥለት ሴት ከእኔ ጋር ወደዚህ አገር ለመምጣት እምቢ ብትልስ? ልጅህን ቀድሞ አንተ ወደነበርክበት አገር እንዲመለስ ላድርገውን?” ብሎ ጠየቀ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 አገልጋዩም፣ “ሴቲቱ ከእኔ ጋራ ወደዚህ ምድር ለመምጣት ፈቃደኛ ባትሆን ምን አደርጋለሁ? ልጅህን አንተ ወደ መጣህበት አገር ልውሰደውን?” ሲል ጠየቀው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ሎሌውም፦ “ሴቲቱ ምናልባት ወደዚህ አገር ከእኔ ጋር ለመምጣት እንቢ ያለች እንደሆነ ልጅህን ወደ ወጣህበት አገር ልመልሰውን?” አለው።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ሎሌ​ውም፥ “ሴቲቱ ምና​ል​ባት ወደ​ዚህ ሀገር ከእኔ ጋር ለመ​ም​ጣት ባት​ወ​ድ​ድስ ልጅ​ህን ወደ መጣ​ህ​በት ሀገር ልመ​ል​ሰ​ውን?” አለው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ሎሌውም፦ ሴቲቱ ምናልባት ወደዚህ አገር ከእኔ ጋር ለመምጣት እንቢ ያለች እንደ ሆነ ልጅህን ወደ ወጣህበት አገር ለመልሰውን? አለው።

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 24:5
8 Referencias Cruzadas  

እኔም ጌታዬን ‘ልጅቷ ከእኔ ጋር ለመምጣት ፈቃደኛ ባትሆንስ ምን ላድርግ?’ ብዬ ጠየቅሁት።


ነገር ግን ወደ ትውልድ አገሬ ሂድ፤ እዚያም ካሉት ወገኖቼ መካከል ለልጄ ለይስሐቅ ሚስት ምረጥለት።”


ስለዚህ ርብቃን ጠሩና “ከዚህ ሰው ጋር መሄድ ትፈልጊያለሽን?” ብለው ጠየቅዋት። እርስዋም “አዎ እሄዳለሁ” አለች።


አብርሃም ግን እንዲህ አለው፤ “በምንም ምክንያት ቢሆን ልጄን ወደዚያ አገር መልሰህ እንዳትወስድ ተጠንቀቅ!


“የአምላክህን የእግዚአብሔርን ስም በከንቱ አታንሣ፤ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚያነሣውን ሁሉ ሳይቀጣው አያልፍም።


ዳግመኛ እምቢ ብትል ግን፥


አስተዋይ ሰዎች ለሚሠሩት ሥራ አስቀድመው ዕቅድ ያወጣሉ፤ ማስተዋል የጐደላቸው ሰዎች ግን አላዋቂነታቸውን ይገልጣሉ።


በእውነትና በቅንነት ‘ሕያው እግዚአብሔርን’ ብላችሁ ብትምሉ ሕዝቦች ይባረካሉ፤ በዚህም ይመካሉ።”


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos